Logo
SeledaPost
ብልፅግና ፓርቲ የተወዳደረባቸውን ወንበሮች በሙሉ አሸነፈ

👉 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወይም የግል ዕጩዎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ)  ምንም መቀመጫ አላሸነፉም።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ከፊል ውጤት እወጃ በስካይ ላይት ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የሌሎች 22 የምርጫ ክልሎችን ውጤት አፅድቆ ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሠረት፣ ከተገለጹት ጠቅላላ 48 የምክር ቤት መቀመጫዎች መካከል ከአንዱ በስተቀር የገዢው ብልፅግና ፓርቲ ዕጩዎች ያሸነፉ ሲሆን፣ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ዕጩ ደግሞ በሶማሌ የክልል ምክር ቤት አንድ ወንበር ማሸነፉ ታውቋል። በደገ ሀቡር አንዱን ወንበር የኦጋዴን ግንባር ዕጩ የነበሩት አቶ መሀሙድ ሀሰን ሁሴን አሸንፈዋል።

ለክልል ምክር ቤቶች በጠቅላላው የ12 የክልል ምክር ቤት የምርጫ ክልሎች ውጤቶች ተነግረዋል። የክልል ምክር ቤት ምርጫዎች በየምርጫ ክልሉ ብዙ መቀመጫዎች ያሏቸው በመሆኑ፣ በድምሩ የ38 መቀመጫዎች ውጤት የታወጀ ሲሆን፣ ከነዚህም ውስጥ ብልፅግና ፓርቲ 37ቱን አሸንፏል።

ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላላው የ10 የምርጫ ክልሎች/ወንበሮች ውጤት የተገለጸ ሲሆን (1 ከአማራ፣ 3 ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና 6 ከኦሮሚያ)፣ 10ሩንም መቀመጫዎች በሙሉ የብልፅግና ፓርቲ ዕጩዎች አሸንፈዋል። ውጤታቸው የተገለጹት የምርጫ ክልሎችም በአማራ ክልል ጎዛምን፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ቀዲዳ ጋሜላ 2፣ ጉመር 1 እና እዣ 2 ሲሆኑ፣ በኦሮሚያ ክልል ደግሞ ሀብሮ 1፣ ቅንበቢት፣ ጥቁር እንጭኒ፣ ጀልዱ፣ ወሊሶ 2 እና ወሊሶ 1 የምርጫ ክልሎች ናቸው።

በውጤት እወጃው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወይም የግል ዕጩዎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ)  ምንም መቀመጫ አላሸነፉም

Seledadotio
Seledadotio
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.