የኮንትሮባንድ እቃዎችን ጭኖ የተገኘ የጭነት ተሽከርካሪ ተወርሶ ለመንግሥት ገቢ እንዲደረግ የሚያዘው አዋጅ በዛሬው ዕለት ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
የኮንትሮባንድ ወንጀል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየረቀቀና በአገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረው ጉዳት እየከፋ በመምጣቱ፣ለሕገ-ወጥ ንግድ ማጓጓዣነት የሚያገለግሉ ተሽከርካሪዎች በቀጥታ እንዲወረሱ የሚደነግግ አዲስ የአዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡ ይታወቃል።
ቀደም ሲል በአዋጅ ቁጥር 1160/2011 በተደረገ ማሻሻያ፣ የተሽከርካሪ ባለቤቶች በወንጀሉ በቀጥታ ካልተሳተፉ ንብረታቸው ከመወረስ ይልቅ 100,000 (መቶ ሺህ) ብር ብቻ ተቀጥተው ንብረታቸውን እንዲረከቡ ይፈቀድ ነበር።
ይሁን እንጂ ይህ አሰራር ኮንትሮባንዲስቶች የተቀመጠውን ቅጣት እንደ ቀላል የሥራ ማስኬጃ ወጪ በመቁጠር የሕገ-ወጥ ንግዱ ይበልጥ እንዲጧጧፍ በር መክፈቱን የተሻሻለው አዋጅ ይገልጻል።
በተጨማሪም ወንጀሉ አሁን ላይ እጅግ የረቀቀ መልክ በመያዙ:-
• ኮንትሮባንዲስቶች መንገድ በሌለባቸው አካባቢዎች በከፍተኛ ፍጥነት የሚሽከረከሩ፣
• ለመለየት የሚያዳግቱ መደበቂያ አካላት የተገጠሙላቸው አልፎ ተርፎም ጎማቸው በጥይት ቢመታ እንኳ እንዳይቆሙ የሚያስችል የጥይት መከላከያ የገጠሙላቸው ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም ላይ መሆናቸው ይገልጻል።
ይህንን ተግዳሮት ለመፍታት አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ጥብቅ ማሻሻያዎች አድርጓል።
በእዚህም መሰረት ማንኛውም ተሽከርካሪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ለመደበቅ እንዲያስችል ሆኖ የተሠራ፣ የተለወጠ ወይም መደበቂያ አካል የተገጠመለት ሆኖ ከተገኘ በቀጥታ ይወረሳል።
አንድ ተሽከርካሪ የጫነው የኮንትሮባንድ ዕቃ መጠን የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ ከተቀመጠው ገደብ በላይ ከሆነ፣ የዕቃው ግምታዊ ዋጋ ከግምት ውስጥ ሳይገባ ተሽከርካሪው ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
አዋጁ የባለቤቶችን መብት ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ተሽከርካሪው ከመወረሱ በፊት ባለቤቱ ጉዳዩን እንዲያውቀውና ተሽከርካሪው ጥቅም ላይ ስለዋለበት ሁኔታ ማስረጃዎችን በማቅረብ ራሱን እንዲከላከል ዕድል እንደሚሰጠውም በድንጋጌው ላይ ተመልክቷል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 24 ኛ መደበኛ ስብሰባውን በነገው ዕለት የሚያካሂድ ሲሆን በስብሰባውም የጉምሩክ አዋጅን አስመልክቶ የፕላን፣በጀተና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን እንደሚያጸድቀው ይጠበቃል።
Seledadotio

2 months ago