Logo
SeledaPost
ምክር ቤቱ ነገ ስብሰባን መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 24ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ በይፋ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያደርገው በዚህ ስብሰባው፣ በሀገሪቱ የኢኮኖሚና የደህንነት ዘርፎች ላይ ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸውን ሁለት ወሳኝ ረቂቅ አዋጆች መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ምክር ቤቱ በቅድሚያ የጉምሩክ አዋጅን እንደገና ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አስመልክቶ፣ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ዝርዝር ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ ይመረምራል።

ይህንን የሪፖርት ግምገማ ተከትሎም ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከፓርላማው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

በተመሳሳይ ሁኔታ ምክር ቤቱ በነገው ዕለት በሚያካሂደው ስብሰባ፣ የሀገሪቱን ዲጂታል ሉዓላዊነት ለመጠበቅ የወጣውን የቁልፍ መሠረተ-ልማቶች የሳይበር ደህንነት ረቂቅ አዋጅን በሰፊው የሚመለከት ይሆናል።

አዋጁን አስመልክቶ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ በጥልቀት ከመረመረ በኋላ፣ ረቂቅ አዋጁን በይፋ እንደሚያፀድቅ ታውቋል።

Seledadotio
Seledadotio
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.