የ80 ቀን መታሰቢያ
#ethiopia | አቤቱ አንተ ለትውልድ ሁሉ መጠጊያ ሆንክልን መዝሙር 89-1 በሚለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል በመጀመር የባለታሪኳ የ80 ቀን መታሰቢያ ተገልጿል።
የሕይወት ታሪካቸው እንደሚጠቁመው ወይዘሮ አዘነጋሽ ኃይሉ በቀድሞው አጠራር በአርሲ ክፍለ ሀገር ቆሬ ቀበሌ በ1951 ዓመተ ምሕረት ከአባታቸው ከአቶ ኃይሉ ደምሴ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ አበራሽ አየለ ተወለዱ።
የትምህርት ዕድሜያቸው ሲደርስ በሻሸመኔ በሚገኘው አፄ ናዓድ ትምህርት ቤት በመግባት ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል የተማሩ ሲሆን በመቀጠልም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሐዋሳ ታቦር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል።
በወቅቱ በነበረው ባህላዊ የቤተሰብ ጋብቻ መሠረት በ1967 ዓመተ ምሕረት ከአቶ መርጊያ ተገኝ ጋር ትዳር መስርተው 2 ወንድና 6 ሴት ልጆችን ለማፍራት በቅተዋል።
ወይዘሮ አዘነጋሽ የቀሰሙትን ትምህርት እንዲሁም ከተፈጥሮ ያገኙትን ዕውቀትና ትዕግስት በማስተባበር ባለቤታቸው በተሰማሩበት የሥራ መስክ ሁሉ ሳይለዩዋቸው በምክርና በማበረታታት አግዘዋል።
በንግዱም ሆነ በግብርናው ዘርፍ ደከመኝ ሳይሉ ሌት ተቅን በመሥራት ባለቤታቸውን የደገፉ ጠንካራ ሴት ነበሩ።
ይሁንና ወይዘሮ አዘነጋሽ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባጋጠማቸው ሕመም ምክንያት በሐዋሳና በአዲስ አበባ በሚገኙ የተለያዩ ሆስፒታሎች ከፍተኛ የሕክምና ክትትል ቢደረግላቸውም ሳይሻላቸው ቆይቶ መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓመተ ምሕረት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ይህ መረጃ የተገኘው ከልጆቻቸው
ከመንበረ መርጊያና ከታጋይ አባይነህ ነው።
#የሕይወትታሪክ #መታሰቢያ #ሐዋሳ #ሻሸማኔ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2 months ago