(ዘ-ሐበሻ ዜና) አቶ ጌታቸው ረዳ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በ35ኛው የነጻነት በዓል ላይ ያደረጉትን ንግግር አስመልክቶ ጠንካራ ትችት ሰንዝረዋል። አቶ ጌታቸው ይህን ትችት ያቀረቡት የአፍሪካ ጉዳዮች ተንታኝ የሆኑት ካሜሮን ሀድሰን በትዊተር)ገጻቸው ያነሱትን ጥያቄ መነሻ በማድረግ ነው። ካሜሮን ሀድሰን በመልእክታቸው፣ ማንኛውም ጤነኛ መሪ የብሔራዊ በዓል መልእክቱን አብዛኛውን ክፍል ስለ ሀገሩ እድገት እና መረጋጋት ከማውራት ይልቅ፣ ለዶናልድ ትራምፕ፣ ለማጋ (MAGA) እና በአሜሪካ ለሚመራው የዓለም አቀፍ ሥርዓት ለምን ይሰጣል? ሲሉ የፕሬዝዳንቱን ንግግር ይዘት ጠይቀው ነበር።
ይህንኑ የሀድሰንን ሀሳብ በማጋራት አቶ ጌታቸው ረዳ ባሰፈሩት ጽሁፍ፣ ይህ ጥያቄ ለብዙ ዓመታት ሲጠየቅ የኖረ መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም፣ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በመፍረስ አደጋ አፋፍ ላይ ያለችን ሀገር ከሚመራ መሪ ይልቅ፣ ለዓለም ማንም ያልጠየቃቸውን ምክር እንደሚለግስ "ፈላስፋ ንጉሥ" ሆነው እንደሚናገሩ ክፉኛ ተችተዋል።
ከዚህም ባሻገር ከከረን፣ ከደቀመሃሪ ወይም ከዓዲ ዃላ ከተሞች ይልቅ በካምፓላ እና በጁባ የሚኖሩ ኤርትራውያን ቁጥር መብዛቱ፣ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ላለፉት 35 ዓመታት ሆን ብለው እና በደስታ ሲያዘጋጁት የነበረውን አጠቃላይ የተስፋ መቁረጥ ስሜት በሚገባ እንደሚያሳይ አብራርተዋል። በመጨረሻም፣ ፕሬዝዳንቱ ትናንትና ለ35ኛ ጊዜ በይስሙላ ሲያከብሩት የነበረውን የኤርትራን ነጻነት ራሱን የሚጠሉት እንደሚመስል አቶ ጌታቸው በመልእክታቸው አስፍረዋል።

10 days ago