Logo
FastMereja
የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ
‎
‎በወላይታ ዞን ዲንቱ ከተማ አስተዳደር በሁለት ተሽከርካሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት እስካሁን የ6 ሰው ህይወት ማለፉ ተገለጸ።
‎
‎አደጋው የተከሰተው ከዲላ ወደ ሶዶ እየተጓዘ የነበረ ዶልፊን ተሽከርካሪ ከወላይታ ሶዶ ወደ ሀዋሳ ሲጓዝ ከነበረ ቅጥቅጥ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨታቸው የተፈጠረ ነው።
‎
‎እስካሁን የዶልፊኑ አሽከርካሪን ጨምሮ የስድስት ሰው ህይወት ማለፉን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያስረዳል።
‎
‎የመረጃ ምንጭ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ነው ።

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.