Logo
SeledaPost
ልደት እና ሞት በወቅቱ በማያስመዘግቡ ነዋሪዎች ላይ 5 ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት ሊጣል ነው

የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከሚቀጥለው በጀት ዓመት (ከሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም.) ጀምሮ እንደ ልደት እና ሞት ያሉ የወሳኝ ኩነት ምዝገባዎችን በወቅቱ በማያስመዘግቡ ነዋሪዎች ላይ የ5 ሺሕ ብር ቅጣት ሊጥል እንደሚችል አስታውቋል።

​የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥጋቡ ሹመይ የማኅበረሰቡን የግንዛቤ ማነስ ከግምት ውስጥ በማስገባት እስካሁን አስገዳጅ የቅጣት ውሳኔዎች ሳይተላለፉ መቆየታቸውን ገልጸው፣ አሁን ግን ደንቡን ተግባራዊ ለማድረግ መታቀዱን  ተናግረዋል።

​እንደ አቶ ጥጋቡ ማብራሪያ፤ ማንኛውም ነዋሪ፦

👉​ልደትን ፦ በ90 ቀናት ውስጥ

👉​ጋብቻ፣ ፍቺ፣ ሞት እና ጉድፈቻ ኩነቶችን ፦ በ30 ቀናት ውስጥ ማስመዝገብ ግዴታ አለበት።

​ነዋሪዎች የተቀመጠውን የጊዜ ቀነ-ገደብ በአግባቡ በመጠቀም ራሳቸውን ካልተፈለገ የገንዘብ ቅጣት እንዲጠብቁም ኤጀንሲው አሳስቧል።

ምንጭ: አሐዱ ራዲዮ

seledadotio
seledadotio
3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.