Logo
FBC
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያዎን ከባንክ ሂሳብዎ ጋር ለማስተሳሰር እነዚህን አማራጮችን ብቻ ይጠቀሙ፦

1. ባሉበት ሆነው id.et/connect ላይ ገብተው የሚፈልጉትን የባንክ ማስተሳሰሪያ ሊንክ በመጠቀም ማስተሳሰር ወይም

2. በአቅራቢያዎ በሚገኝ የባንክ ቅርንጫፍ በመሔድ ማስተሳሰር ይችላሉ።

👉 ከኢትዮጵያ ውጪ የሚገኙ ዜጎች የባንክ ሂሳባቸውን ከፋይዳ ጋር እንዴት ያስተሳስራሉ?

በምዝገባ ወቅት የኢሜይል አድራሻ ካልሞሉ id.et/update (http://id.et/update) ላይ በመግባት የኢሜይል አድራሻዎን መጨመር/ መረጃዎን ማዘመን ይችላሉ።

የባንክ ሒሳብዎን ከፋይዳ ጋር ለማስተሳሰር የሚላክ የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል (OTP) ስልክ ቁጥር አጠገብዎ በማይኖርበት ሁኔታ በኢሜይል አድራሻዎ ይደርስዎታል።

ሊያስተውሏቸው የሚገቡ ጉዳዮች፡-

👉 ከባንክ ወይም ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (ፋይዳ) በስልክ ተደውሎ የሚደረግ ምንም አይነት የማስተሳሰር ስራ የለም። ተቋሙን አስመስለው በስልክዎ በመደወል እናስተሳሰርላችሁ የሚሉ ጥሪዎች ተቀባይነት ስለማይኖራቸው፤ መረጃዎን አያጋሩ።

👉 የባንክ ሂሳብ ቁጥርዎን፣ የፋይዳ ቁጥርዎን እንዲሁም የይለፍ ቃሎችን (PASSWORDS) ለማንም ማጋራት የለብዎትም።

👉 “ፋይዳ መታወቂያዎን ከባንክ ጋር ለማስተሳሰር ይህን ሊንክ ይጫኑ” የሚሉ ትክክለኛ መሆናቸው የሚያጠራጥሩ የባንክ እና የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (ፋይዳ) መሰል የፅሁፍ መልዕክቶችን መክፈት የለብዎትም።

👉 ባሉበት ሆነው ለማስተሳሰር https://id.et/connect ላይ ይግቡ።

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.