(ዘ-ሐበሻ ዜና) ወደፈረንሳይ ሊላክ የነበረው ኤርትራዊ እንግሊዝ እስር ቤት ውስጥ ራሱን የማጥፋት ሙከራ አደረገ፡፡ ዘጋርዲያን ጋዜጣ እንደዘገበው ይህ ኤርትራዊ ‹‹ዋን ኢን፣ ዋን አውት›› በተሰኘው ፕሮግራም መሰረት ከእንግሊዝ ተጠርዞ ወደፈረንሳይ እንዲሄድ ትኬት ተቆርጦለት ነበር፡፡ በእንግሊዝ እስር ቤት ውስጥ ተቀምጦ የሚጓዝበትን ቀን በመጠባበቅ ላይ እያለ ግን ራሱን የማጥፋት ሙከራ አድርጓል፡፡
ወደፈረንሳይ ቢሄድ አደጋ እንደሚገጥመው የሰጋው ይህ ኤርትራዊ ራሱን ለማጥፋት እየሞከረ መሆኑን የተናገሩት አብረውት የታሰሩት ሰዎች መሆናቸውን የገለፀው ዘገባው በዚህ የተነሳም የተቆረጠለት የአውሮፕላን ትኬት መሰረዙን አስረድቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት በእስር ቤቱ ውስጥ ተመሳሳይ አደጋ በራሱ ላይ እንዳያደርስ በካቴና ታስሮ የቅርብ ክትትል እየተደረገለት ይገኛል፡፡ ይህ ኤርትራዊ ወደፈረንሳይ ተጠርዞ ሊላክ የነበው ባለፈው አመት እንግሊዝና ፈረንሳይ ያደረጉትን ስምምነት ተከትሎ ነው፡፡
በስምምነታቸው መሰረት እንግሊዝ ከፈረንሳይ በጀልባ አቋርጦ እንግሊዝ የገባ አንድ ጥገኝነት ጠያቂን ወደፈረንሳይ ስትልክ ፈረንሳይ ደግሞ በጀልባ የማቋረጥ ሙከራ ያላደረገ አንድ ስደተኛን ወደእንግሊዝ ትልካለች፡፡ በዚህ መሰረትም ባለፉት 8 ወራት 605 ስደተኞች ወደፈረንሳይ ሲላኩ 581 ደግሞ ወደእንግሊዝ ለመግባት ችለዋል፡፡ ሁለቱ አገራት ይህንን ስምምነት ያደረጉት ከፈረንሳይ ወደእንግሊዝ በአነስተኛ ጀልባ የሚደረገውን አደገኛ ጉዞ ለማስቀረት በሚል ነው፡፡ ይሁንና ባለፈው ሳምንት ብቻ በ3 ጀልባዎች 196 ሰዎች ይህንን መንገድ አቋርጠው እንግሊዝ ገብተዋል፡፡

14 days ago