(ዘ-ሐበሻ ዜና) ቻይና እና ሩሲያ የኢራንን ከፍተኛ መጠን ያለው የበለጸገ ዩራኒየም ደህንነት ለማረጋገጥ እና ለማከማቸት በድርድር ላይ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገለጸ።
በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢራን ጉዳዮች ጊዜያዊ ዳይሬክተር የነበሩት ጆይ ሁድ ለአልጀዚራ እንደተናገሩት፣ የኢራን ከፍተኛ መጠን ያለው የበለጸገ ዩራኒየም ከአሜሪካ ጋር ለሚደረግ ማንኛውም የሰላም ስምምነት "የሁሉም ነገር ቁልፍ" ነው። ዳይሬክተሩ አክለውም፣ 441 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የኢራን ዩራኒየም እስከ 60 በመቶ የበለጸገ በመሆኑ ለሲቪል (ሰላማዊ) አገልግሎት የሚውልበት ምንም ዓይነት ዕድል እንደሌለው እና ለወታደራዊ የጦር መሳሪያ ማምረቻ ብቻ ሊያገለግል እንደሚችል አስረድተዋል።
በመሆኑም "በመጨረሻ ሩሲያ እና ቻይናም ቢሆኑ ይህ ዩራኒየም ከኢራን ወጥቶ ደህንነቱ በተጠበቀ ስፍራ እንዲቀመጥ (ወደ እነርሱ እንዲዘዋወር) መስማማታቸው አይቀርም" ብለዋል።
የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ እና የሩሲያው ቭላድሚር ፑቲን በዚህ ሳምንት ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት የኢራንን ዩራኒየም ስለመረከብ እና ማከማቸት ጉዳይ ተነጋግረው ሊሆን እንደሚችል ጆይ ሁድ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። "በቤጂንግ በዚህ ጉዳይ ላይ ጸጥ ያለ (ሚስጥራዊ) ውይይት ተደርጎ ሊሆን ይችላል፤ ምናልባትም ከኢራናውያን ጋርም እየተነጋገሩ ይሆናል። ይህንን ወደፊት የምናየው ይሆናል" በማለት ሁኔታውን አብራርተዋል።

3 months ago