የአርሰናል የዋንጫ ማስተናገጃ ዕለት የትኬት ዋጋ ሰማይ ነክቷል!
#ethiopia | ከ22 ዓመታት ረጅም ጥበቃ በኋላ የዘንድሮውን የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ማሳካቱን ያረጋገጠው አርሰናል፣ እሁድ ዕለት ከክሪስታል ፓላስ ጋር የሚያደርገው የዓመቱ የመጨረሻ ጨዋታ በክለቡ ታሪክ ከፍተኛ የትኬት ዋጋ የተመዘገበበት ሆኗል።
መድፈኞቹ ዋንጫቸውን በይፋ በሚረከቡበት በዚህ ታሪካዊ ጨዋታ ላይ ለመገኘት ደጋፊዎች በከፍተኛ ፉክክር ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣ በጥቁር ገበያ (በመልሶ ሽያጭ ድረ-ገጾች) ላይ የወጡ የትኬት ዋጋዎች አስገራሚ መናር አሳይተዋል።
በአሁኑ ሰዓት በበይነ-መረብ ላይ ለሽያጭ ከቀረቡት ትኬቶች መካከል ዝቅተኛው ዋጋ 3,000 የእንግሊዝ ፓውንድ የደረሰ ሲሆን፣ በክብር መቀመጫዎች አካባቢ ያሉ ምርጥ ቦታዎች ደግሞ እስከ 45,000 ፓውንድ እየተጠየቀባቸው ይገኛል።
ይህ እብደት የተሞላበት የዋጋ ጭማሪ የደጋፊዎችን የዋንጫ ናፍቆትና የታሪኩ አካል ለመሆን ያላቸውን ጉጉት በግልጽ ያሳየ ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#arsenal #eplchampions #crystalpalacevsarsenal #ticketprices #premierleague #gunners #footballnews #getutemesgenmedia

14 days ago