Logo
EBC
ኢትዮጵያ እና ኳታር የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ አጋርነት ለመገንባት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገለጹ
*****************

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ ከኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ መሐመድ ቢን አብዱልራህማን ቢን ጃሲም አል ታኒ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅት በኢትዮጵያ እና በኳታር መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

ሁለቱ ወገኖች መደበኛ የፖለቲካ ምክክሮችን በማድረግ፣ የኢኮኖሚ ትብብርን በማጠናከር እና የግል ዘርፍ ኢንቨስትመንትን በማሳደግ ረገድ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ አጋርነት ለመገንባት ያላቸውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም በአፍሪካ ቀንድ፣ በባህረ ሰላጤው ቀጣና እና ከዚያም ባሻገር ቀጣናዊ ሰላምና ደህንነትን ለማስፈን የሚደረጉ የጋራ ጥረቶችን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
#ethiopia #qatar #bilateral #partnership #ebc

16 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.