3 days ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የእንኳን አደረሰዎት መልዕክት አስተላለፉ
********************
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ በመንግሥት አስተዳደር ውስጥ ለ25 ዓመታት በማገልገል የብር ኢዮቤልዩአቸውን እያከበሩ ላሉት የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የእንኳን አደረሰዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ናሬንድራ ሞዲ እአአ ከ2001 እስከ 2014 የጉጃራት ግዛት ዋና አስተዳዳሪ፣ ከዚያ ወዲህ ደግሞ የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመልዕክታቸው፣ የኢትዮጵያ እና የሕንድ አጋርነት ባለፉት ዓመታት ይበልጥ እየተጠናከረ መምጣቱን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል እንድትሆን ሕንድ የሰጠቻትን ድጋፍ እንዲሁም ናሬንድራ ሞዲ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት በማሳያነት ጠቅሰዋል።
አያይዘውም፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ሁለንተናዊ አጋርነት ይበልጥ ለማሳደግ ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል።
#ትልቅ_ሀገር ! #ትልቅ_ሕዝብ ! #ታላቅ_ርዕይ !
#ethiopia #india #bilateral #partnership #abiyahmed #narendramodi #ebc

4 months ago
ኢትዮጵያ እና ኒውዚላንድ በWTO አባልነት ሂደት የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ስምምነት ተፈራረሙ
#ethiopia | ጄኔቫ፣ ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. – ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) አባል ለመሆን በምታካሂደው የድርድር ሂደት አካል የሆነውን የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ፕሮቶኮል (Bilateral Market Access Protocol) ከኒውዚላንድ ጋር ተፈራርማለች።
ስምምነቱ ኢትዮጵያ ወደ ዓለም አቀፉ የባለብዙ ወገን የንግድ ሥርዓት ለመቀላቀል በምታደርገው ጉዞ ታሪካዊ ምዕራፍ መሆኑ ተገልጿል። ለረጅም ጊዜ ሲካሄድ የነበረውን የሁለትዮሽ ድርድር ያጠናቀቀው ይህ ፕሮቶኮል፣ በሸቀጦችና በአገልግሎቶች ዘርፍ ላይ የጋራ የገበያ ተደራሽነት ግዴታዎችንና ጥቅሞችን ያካትታል።
ስምምነቱን በጄኔቫ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ፀጋአብ ከበበው እና በWTO የኒውዚላንድ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ክሌር ኬሊ ፈርመውታል።
በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ሁለቱ አገራት ግልጽነትን፣ በሕግ የሚመራ ሥርዓትን እና ልማትን ማዕከል ያደረገ የባለብዙ ወገን የንግድ ሥርዓት ለመገንባት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
የኒውዚላንድ ተወካይ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገበች ያለች አገር መሆኗን በማንሳት፣ የWTO አባል መሆኗ ከዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ጋር ያላትን ትስስር የበለጠ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል። በተጨማሪም አገራቸው የኢትዮጵያን የWTO አባልነት ሂደት በመደገፍ ረገድ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጣለች።
አምባሳደር ፀጋአብ ከበበው በበኩላቸው፣ ኒውዚላንድ በድርድሩ ሂደት ሁሉ ላሳየችው ገንቢ ተሳትፎ እና ቀጣይነት ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ከንግድ ግንኙነቱ ባሻገር፣ ኢትዮጵያ እና ኒውዚላንድ በግብርና፣ በጂኦተርማል ኃይል ልማት እና በቴክኒክ አገልግሎቶች ዘርፍ ያላቸውን ትብብር እያጠናከሩ ሲሆን፣ ይህ ስምምነት በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የንግድና የኢንቨስትመንት ግንኙነት የበለጠ እንደሚያሳድግ ይጠበቃል።

5 months ago
ኢትዮጵያ እና ኳታር የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ አጋርነት ለመገንባት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገለጹ
*****************
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ ከኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ መሐመድ ቢን አብዱልራህማን ቢን ጃሲም አል ታኒ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።
በውይይቱ ወቅት በኢትዮጵያ እና በኳታር መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
ሁለቱ ወገኖች መደበኛ የፖለቲካ ምክክሮችን በማድረግ፣ የኢኮኖሚ ትብብርን በማጠናከር እና የግል ዘርፍ ኢንቨስትመንትን በማሳደግ ረገድ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ አጋርነት ለመገንባት ያላቸውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል።
በተጨማሪም በአፍሪካ ቀንድ፣ በባህረ ሰላጤው ቀጣና እና ከዚያም ባሻገር ቀጣናዊ ሰላምና ደህንነትን ለማስፈን የሚደረጉ የጋራ ጥረቶችን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
#ethiopia #qatar #bilateral #partnership #ebc

11 months ago
የኢትዮጵያ"የሀይል ማስፋት" (Power Projection)፡በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የዲፕሎማሲ ጥረት...!
(የሀብታሙ ደባሱ አዲሱ የግል ሀሳብ )
#ethiopia | በቅርቡ የተከናወነው በደቡብ አፍሪካ አዘጋጅነት የG-20 የኢትዮጵያ ተሳትፎ እንዲሁም የማሌዥያና የሲንጋፖር መሪዎች ጉብኝት፣የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መንግስት እየተከተለው ያለውን የዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ "የሀይል ማስፋት"ስትራቴጂ ቁልፍ ማሳያዎች ናቸው።ይህ ስትራቴጂ ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተጽዕኖ በማስፋት፣ለሀገር ውስጥ ዕድገት የሚያስፈልገውን ሀብትና ዕውቀት ለመሳብ ያለመ መሆኑን ያሳያል።
🔴 የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዲፕሎማሲያዊ ራዕይ፦
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በዋናነት በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ (Economic Diplomacy) እና የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን በማስፋት ላይ ያተኮረ ነው።ከዓለም ደቡብ (Global South) አገሮች በተለይም ከእስያ እና ከመካከለኛው ምስራቅ ጋር አዲስና ጠንካራ ስትራቴጂካዊ አጋርነት መገንባት፤ በሁሉም ወገን የሀገርን መሰረታዊ ብሄራዊ ጥቅም ማስከበር እና ማረጋገጥ አጋርነትን ማስፋትን ያካትታል።
የ"ብልጽግና" ጽንሰ-ሀሳብ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች በሙሉ ከብልጽግና ራዕይ ጋር የተሳሰሩ ሲሆን፣ የውጭ ግንኙነት በዋናነት ለሀገር ውስጥ ኢኮኖሚ ዕድገት እና ለሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲያገለግል ለማድረግ ያለመ ነው።
🔴የቡድን ሀያ አባለ ሀገራት (G-20) ተሳትፎ፦የብዙ-ዋልታ ዓለምን (Multipolar World) መቀበል ኢትዮጵያ በG-20 ስብሰባ ላይ እንደ ልዩ እንግዳ መሳተፏ፣በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራው ዲፕሎማሲ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ቀንድ ባሻገር ዓለም አቀፋዊ ተዋናይ አድርጎ ለማስቀመጥ ያለውን ጥረት ያሳያል።በዓለም የፋይናንስ እና የፖለቲካ ውሳኔ ሰጪ ማዕከላት ላይ ድምጽ እንዲኖራት ማድረግ።ክቡር ዶ/ር ዐቢይ በተደጋጋሚ እንደሚገልጹት፣ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኀብረት ዋና መስሪያቤት መቀመጫ እንደመሆኗ መጠን የአፍሪካን አጠቃላይ ጥቅም በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ በማንሳት፣ የሀይል ማስፋት ጥረቷን ከአህጉራዊ ሚናዋ ጋር አጣምራለች።
🔴 የእስያ መሪዎች ጉብኝት፦የቴክኖሎጂና የኢንቨስትመንት ድልድይ የማሌዥያ እና የሲንጋፖር መሪዎች ጉብኝት የዶ/ር ዐቢይ የዲፕሎማሲ ጥረት ዋነኛ መገለጫ ነው።ከእነዚህ ፈጣን ዕድገት ካላቸው የእስያ "ነብሮች" (Asian Tigers) ጋር ግንኙነት መፍጠር የኢትዮጵያን የመበልፀግ የማደግ ስትራቴጂ ለመደገፍ ወሳኝ ነው።
🖊እንደ መውጫ ስልታዊ ትኩረት የሀይል ማስፋት ትርጉም⁉️
ሲንጋፖር የላቀ የሎጅስቲክስ አስተዳደር፣ ዘመናዊ የከተማ ልማት (Smart City)፣ የዲጂታል ኢኮኖሚ ልምድ ሽግግር፤ የኢትዮጵያን የባህር በር ፈተና ለመቅረፍ ዘመናዊ የንግድ መስመሮችን መገንባት እንደ አስረጅነት ይጠቀሳል ።( በሀገራችን በአዲስ አበባ እና በሌሎች ክልል ከተሞች እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ፤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ይጠቀሳል ።
ማሌዥያ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት (FDI) በኤሌክትሮኒክስና በኢንዱስትሪ ዘርፍ መሳብ፣ የዘይትና ዘይት ነክ ምርቶች ንግድ በማጠናከር የኢኮኖሚ አጋርነትን እና የንግድ አጋሮች ማጎልበትን ያሳያል ።( Industrial Park Development cooperation ስር የሚከናወኑ የእውቀት እና የኢንዱስትሪ ሽግግር መጥቀስ ይቻላል ።)
🔴የማጣቀሻዎች (Reference )
1️⃣Abiy Ahmed (PhD). Medemer: A Collective Journey. (የዶ/ር ዐቢይ የፍልስፍና መሰረት ለዲፕሎማሲያዊ ስትራቴጂያቸው።)
2️⃣ Minister's Office. Official Press Releases on G20 and Bilateral Visits. (የጉብኝቶቹን ዓላማ እና የተደረጉትን ስምምነቶች ለመረዳት።)
3️⃣Think Tank Analysis. ISS, Chatham House or Brookings papers focused on Ethiopia's shift in foreign policy towards Asia and Global South engagement.
ይህ የሚያሳየው የኢትዮጵያ የሀይል ማስፋት እቅድ በዶ/ር ዐቢይ አህመድ መሪነት ኢኮኖሚን ማዕከል ባደረገ እና በብዙ-ዋልታ ትብብር ላይ በተመሰረተ ዘመናዊ ዲፕሎማሲ እየተመራ መሆኑን ያሳያል ።
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መሳካት የድርሻዬን እወጣለሁ !
#ethiopia
ለበለጠ ወዳጅነት የፃሃፊውን የኤክስ(X) እና የፌስቡክ ገፅ ይከታተሉ :-
🔗የኤክስ(X)ገፅ:-tps://x.com/HDebasu?t=WkEcsELrZrHGV1UGX3oSMg&s=09
🔗የፌስቡክ:-https://www.facebook.com/s...

Sponsored by
Surafel
11 months ago
የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር-በር ጥያቄን የሚደግፉ የዓለም አቀፍ ግንኙነት(IR)ህልዩቶች
(የሀብታሙ ደባሱ አዲሱ የግል ሀሳብ)
#ethiopia | የኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር በር አቅርቦት ጥያቄ በዓለም አቀፍ ግንኙነት(IR)ህልዮት መሠረት ሲታይ ምን ይመስላል፤የሚለውን በዛሬው አጭር ፁሁፍ በሪያሊዝም፣በሊበራሊዝም፣እንዲሁም በኮንስትራክቲቪዝም በዋናነት በሦስት ትልልቅ የትንተና ማዕቀፎች ለማብራራት እሞክራለሁ፤በእርግጥ እነኝህ ንድፍ ሀሳቦች በእጅጉ ሰፊ ናቸው። የፖለቲካ ሳይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሊቃውንት በጉዳዩ ላይ ልዩ ልዩ የክርክር እና ሀሳብ መር ውይይት እና መነሻ ፁሁፍ በማቅረብ የሀሳቡን ደርዝ እንዲያሰፉት እጠይቃለሁ ።
🔴ሪያሊዝም ህልዮት(Realism Theory):-
ይህ ህልዮት ቀዳሚ እና የነገረ-ሀሳብ ማንጠሪያ መነፀር ነው፤ዓለም አቀፍ ሥርዓት(International System) የትርምስ ዓለም የሰፈነበት (Anarchic World)ሲሆን፣መንግሥታት ዋነኛ ዓላማቸው ህልውናን ማስጠበቅ እና ኃይልን ማሳደግ ነው።መልካ-ምድራዊ አቀማመጥ የኃይል ምንጭ ወይም ድክመት ነው ብለው ያምናሉ።የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር በር አቅርቦት ጥያቄ ሪያሊዝም ንድፈ-ሀሳብ የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ እንደ ምክንያታዊነት የደህንነት እርምጃ ይደግፈዋል።
የደህንነት ስጋት እና የተዘጋ-መሬት (የመልካ-ምድር እስረኝነት) መሆን የአንድን ሀገር ደህንነት በጎረቤቶች ጥገኛ ስለሚያደርግ "የህልውና አደጋ ነው።የባህር-በር ማግኘት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት እና ስትራቴጂካዊ ራስን የመወሰን አቅም ያጠናክራል።የኃይል ሚዛን( Power of Balance)የቀይ ባህር አካባቢ ወሳኝ የጂኦ-ፖለቲካዊ ውድድርና ፉክክር ቀጠና ስለሆነ፣የባህር በር ማግኘት የኢትዮጵያን ቀጠናዊ ኃይል ያሳድጋል እና የውጭ ጫናን የመቋቋም አቅም ያጎለብታል ።
🔴ሊበራሊዝም ህልዮት (Liberalism Theory):-የዚህ ዋና መርህ በዓለም አቀፍ ትብብር፣በኢኮኖሚ ትስስር እና በዓለም አቀፍ ሕግና ተቋማት አማካኝነት የጋራ ጥቅምን ማሳደግ ይቻላል የሚል ትንታኔ ያቀርባል።የጥያቄው ድጋፍ በሊበራሊዝም የኢትዮጵያን ፍላጎት በኢኮኖሚና በዓለም አቀፍ ትብብር አንፃር ይደግፋል፤ያበረታታል።ከኢኮኖሚ ጥቅም(በጋራ ማደግ) አንፃር ስንመለከተው የባህር-በር ማግኘት የንግድ ወጪን በእጅጉ በመቀነስ የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ያፋጥናል፣ይህም በዓለም አቀፍ የንግድ ስርዓት ውስጥ የተሻለ ተሳትፎ እንድታደርግ ያስችላታል።
የጋራ ተጠቃሚነት መሰረት ያደረገ ችግሩ በኃይል ሳይሆን( Bilateral and Multilateral በሁለትዮሽ ወይም በብዙ ወገን ስምምነቶች፣በጋራ ልማት እና በኢኮኖሚ ትብብር(ለምሳሌ የአፍሪካ ቀንድ የኢኮኖሚ ኮሪደርን በመፍጠር ለዚህም ኢትዮጵያ ለኢኮኖሚያዊ ውህደት እያበረከተች ያለውን ተግባራት መመልከት ይቻላል) አለመግባባቶችን በመፈታት በመጠቆም ጥያቄውን ሰላማዊ መፍትሔ ይሰጣል የሚል አስረጅ ያቀርባል ።
🔴ኮንስትራክቲቪዝም ህልዮት (Constructivism Theory ):-የዚህ ህልዮት ስለ ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች የሚያቀነቅነው የሀገር ማንነትን የሚቀርጹት በቁሳዊ ኃይል ሳይሆን በሀሳቦች፣ በማንነት፣ በባህልና በማኅበራዊ ትርክቶች ነው የሚል እሳቤ ያነሳል የጥያቄው ድጋፍንም ይህ ንድፈ-ሀሳብ የጥያቄውን መነሻ ከብሔራዊ ስሜት አንፃር ያብራራል።
ኢትዮጵያ በታሪክ ስሪት ቀዳሚ እና ከቅድመ-አያቶቻችን ጀምሮ በስፍራው የነበረን የላቀ ተሳትፎ እና ኢትዮጵያ የነበራት የንግድና መርከቦች እንዲሁም የሰዎች እንቅስቃሴ ከፍተኛ መሆኑን እንመለከታለን ይህን የታሪክ ድልድይ ከአሁን ዘመን ትውልድ ጋር የማንነት ግንባታ ይፈጥራል።መንግስት የባህር በርን እንደ "ታሪካዊ መብት" እና "የህልውና ጉዳይ" አድርጎ ማቅረቡ የዜጎችን የህብረት ስሜት እና የጋራ ማንነት ይቀርጻል፤ፍላጎቱ የሚፈጠረው በሀይል ስሌት ሳይሆን በታሪክ እና በብሔራዊ ክብር ትርክት እንደሆነ ያሳያል።
🖊እንደ መውጫ:-
በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር በር አቅርቦት ጥያቄ በዋናነት በሪያሊዝም(ለደህንነትና ኃይል) እና በሊበራሊዝም(ለኢኮኖሚ ትብብር እና በጋራ መልማት) ኮንስትራክቲቪዝም ህልዮት(የሀገር ማንነትን መቅረፅ) ንድፈ-ሀሳቦች ጠንካራ ድጋፍ ያገኛል።በመሆኑ የብሔራዊ ጥቅም እሴቶችን በመያዝ በትብብር እና የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት በማድረግ በዜጎች ትብብር እና አንድነት ጥያቄው ወደ ልማት እና ኢትዮጵያን ወደ ሃያልነት የሚመልስ እንደሆነ እንገነዘባለን ።
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መሳካት የድርሻዬን እወጣለሁ !
#ethiopia
ለበለጠ ወዳጅነት የፀሃፊውን የኤክስ(X)ገፅ ይከታተሉ :-
https://x.com/HDebasu?t=Bz...

Comments