(ዘ-ሐበሻ ዜና) ሩሲያ ከ64 ሺህ በላይ ወታደሮች የሚሳተፉበት የኒውክሌይር ጦር መሳሪያ ልምምድ ማድረግ ጀመረች፡፡ የሩሲያ መከላከያ ሀይል በአይነቱ ትልቅ የሚባል የኒውክሌይር ጦር መሳሪያ ልምምድ ዛሬ መጀመሩን አስታውቋል፡፡
ለ3 ቀናት በሚቆየው በዚህ ልምምድ ላይ ከ64,000 በላይ ወታደሮችና ከ7,800 በላይ የጦር መሳሪያዎች፣ ወታደራዊ ቁሳቁሶችና ተሸከርካሪዎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል፡፡ ከእነዚህ መካከል 200 ሚሳኤል ማስወንጨፊያዎች፣ ከ140 በላይ የጦር ጀቶች፣ 73 ጀልባዎች፣ 13 ባህር ሰርጓጆችና ስምንት ሚሳኤል ተሸካሚ ባህር ሰርጓጅ መርከቦች እንደሚገኙበት የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር አስረድቷል፡፡
እንደመግለጫው በዚህ ልምምድ ላይ የተለያዩ አይነት የባለስቲክና ክሩዝ ሚሳኤሎችን የማስወንጨፍ ሙከራም የሚከናወን ሲሆን አላማውም ‹‹ወረራ የሚከሰት ከሆነ የጦር ሀይሉ በኒውክሌይር ጦር መሳሪያ ብቃት ያለው እንዲሆን ለማዘጋጀት›› መሆኑን ገልጿል፡፡ በዚህ ልምምድ ወቅት በቤላሩስ በተቀመጠው የኒውክሌይር ጦር መሳሪያ ጥምር ስልጠና የሚከናወን ይሆናል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የቤላሩስ መከላከያ ሀይል በበኩሉ ከሩሲያ ጋር በመሆን የኒውክሌይር ጦር መሳሪያ ልምምድ እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ይህ ልምምድ የተጀመረው የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በቻይና ጉብኝት በሚያደርጉበት ወቅት ነው፡፡

3 months ago