(ዘ-ሐበሻ ዜና) ግብፅና ኤርትራ በቀይ ባህር ላይ የሁለቱን አገራት ወደቦች የሚያገናኝ የመርከቦች መንገድ ለመስራት ተስማሙ፡፡ ግብፅ በዛሬው እለት ከኤርትራ ጋር የተለያዩ ስምምነቶችን ተፈራርማለች፡፡ ከእነዚህ ስምምነቶች መካከል በቀይ ባህር ላይ የሁለቱን አገራት ወደቦች የሚያገናኝ የመርከቦች መንገድ መስራት አንዱ ሲሆን በተጨማሪም ግብፅ በባቡር፣ በወደብና በማሪታይም ላይ ለኤርትራ ልምዷን ለማካፈል የሚያስችል ስምምነትም ፈፅመዋል፡፡
ይህ እንዳለ ሆኖ በተለይ በማእድን፣ በትራንስፖርት፣ በመድሀኒትና በአሳ ምርቶች ላይ የሁለቱን አገራት የኢኮኖሚና ንግድ ትብብር ለማሳደግ የሚያስችል ስምምነት ላይም ደርሰዋል፡፡ እነዚህ ስምምነቶች ሊፈፀሙ የቻሉት ከፍተኛ የግብፅ ባለስልጣናት ወደአስመራ መጓዛቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ወደዚያው የተጓዙት የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በድር አልአቲና የትራንስፖርት ሚኒስትሩ ሌተና ጄኔራል ካሚል አል ዋዚር ሲሆኑ ከፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተገናኝተው መክረዋል፡፡

19 days ago