Logo
SeledaPost
በኢትዮጵያ ኩርሙክ ከተማ ሱዳን ፈፀመችው በተባለ የድሮን ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች ሲገደሉ በእርዳታ ሰጪዎች ላይ ጉዳት ደረሰ!

ከሱዳን ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ኩርሙክ ወረዳ ኩርሙክ ከተማ ውስጥ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት፣ አንድ የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) የሥራ ባልደረባን ጨምሮ ቢያንስ ስምንት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውንና ሌሎች በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች እና የአካባቢው የጤና ባለሥልጣናት ገለጹ።

ነዋሪዎች ጥቃቱ የተፈጸመው ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 5:00 ገደማ መሆኑንና ከአሶሳ ከተማ 94 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የኩርሙክ ከተማ የሰዎች እንቅስቃሴ በሚበዛበት አካባቢ ላይ ማረፉን ተናግረዋል።የዓይን እማኞች ድሮኑ የመጣው ከሱዳን ብሉ ናይል ግዛት አቅጣጫ መሆኑን ጠቅሰው፣ የሱዳን ጦር ከፈጣን ድጋፍ ኃይሎች (RSF) ጋር እያካሄደ በነበረው ግጭት ወቅት ጥቃቱን እንደፈጸመ አስረድተዋል።

seledadotio
seledadotio
3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.