(ዘ-ሐበሻ ዜና) ኢራን የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን (ዩኤኢ) በማስጠንቀቅ፣ አሁን ላይ በተቋረጠው የአሜሪካ እና እስራኤል ዘመቻ በተፋፋመበት ወቅት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ አቡዳቢን መጎብኘታቸውን አስቀድማ ታውቅ እንደነበር ገለጸች።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በኤክስ ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ፣ “ኔታንያሁ አሁን በይፋ ያረጋገጡት፣ የኢራን የደህንነት ተቋማት ከረጅም ጊዜ በፊት ለመሪዎቻችን ያደረሱትን መረጃ ነው” ብለዋል። ይሁን እንጂ፣ ሚኒስትሩ ኢራን ይህን የስለላ መረጃ ከሳምንታት በፊት ለምን ይፋ ሳታደርግ እንደቆየች የሰጡት ማብራሪያ የለም።
አራግቺ አክለውም “ከታላቁ የኢራን ህዝብ ጋር ጠላትነት መፍጠር ሞኝነት የተሞላበት ቁማር (አደገኛ ሙከራ) ነው” ያሉ ሲሆን፣ “ይህን ለማድረግ ከእስራኤል ጋር ማሴር ደግሞ ፈጽሞ ይቅር የማይባል ተግባር ነው” ሲሉ አጥብቀው አስጠንቅቀው "መከፋፈልን ለመፍጠር ከእስራኤል ጋር የሚያሴሩ አካላት በሙሉ ተጠያቂ ይሆናሉ" በማለት ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጠንከር ያለ መልእክት አስተላልፈዋል።

22 days ago