Logo
Getu Temesgen
ኢትዮጵያዊ ባህላችንና እሴታችን

* ሃዘንተኛን ማጽናናትና መደገፍ

#ethiopia | የሟች ቤተሰቦችን የመደገፍና የማጽናናት ኢትዮጵያዊ እሴት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለጠ

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በአንድ የፖሊስ አባል ህይወታቸው ያለፈው የአቶ ተገኝ ባልቻን ቤተሰቦች የአዲስ አበባ አስተዳደር እያጽናና እንደሚገኝ አስታውቋል።

አስተዳደሩ በገባው ቃል መሰረትም ለሟች ቤተሰቦች የመኖሪያ ቤትና የመስሪያ ቦታ ርክክብ አድርጓል።

በስነስርዓቱ ላይ የሟች ቤተሰቦችና የሀገር ሽማግሌዎች የተገኙ ሲሆን ቤተሰቦቹም አስተዳደሩ ከጎናቸው በመሆን ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

በወቅቱ የተገኙት የአዲስ አበባ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ዶክተር ማሾ ኦላና እንደገለጹት አጋጣሚውን ለፖለቲካ ትርፍና ለተዛባ አጀንዳ ለመጠቀም የሚሞክሩ አካላት ከእውነታው የራቁ ናቸው ብለዋል።

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በበኩላቸው መሰል ድንገተኛ ክስተቶችን በሀገር በቀል እሴቶች መፍታት እንደሚገባ ገልጸው በሰው መርዶ ፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት መሞከር ከባህላችን ያፈነገጠ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል።

በመጨረሻም ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን በመመኘት ከህዝብ ጋር በልማትና በጸጥታ ጉዳዮች ላይ ተባብሮ የመስራቱ ተግባር እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
#gulele #addisababa #humanity #ethiopianvalues #communitysupport #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.