Logo
Getu Temesgen
አሜሪካ ክሎድን ለኢትዮጵያ ክፍት አደረገች
#ethiopia | ​የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር አዲስ የምስራች ተሰምቷል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ የማሰብ ብቃትና ውጤታማነቱ የሚታወቀውና በአሜሪካው አንትሮፒክ (Anthropic) ተቋም የሚበለጽገው ክሎድ (Claude) የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) አገልግሎት፣ ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ በይፋ ሥራ መጀመሩን አስታውቋል።

​ይህ ትልቅ እመርታ እንዲመዘገብ የኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት ከአሜሪካው የምርምር ተቋም ጋር ሲያደርግ የነበረው ተከታታይና ውጤታማ የዲፕሎማሲ ውይይቶች ከፍተኛውን ሚና ተጫውተዋል።

ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የሚገኙ የቴክኖሎጂ አፍቃሪዎች፣ የሶፍትዌር አበልጻጊዎችና ተመራማሪዎች እነዚህን የላቁ የ-AI መሣሪያዎች በቀጥታ ለመጠቀም የነበረባቸውን ፈተና አሁን ላይ በይፋ ተፈቷል።

​ኢትዮጵያ በአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ መካተቷ ተጠቃሚዎች የክሎድን የላቀ የኮዲንግ ብቃት፣ ጥልቅ የዳታ ትንተና እና ውስብስብ የምርምር ሥራዎችን በቀላሉ እንዲያከናውኑ ሰፊ የዕድል በር ከፍቶላቸዋል።

ይህም የሀገሪቱን የዲጂታል ምህዳር ከማሳደግ ባለፈ ለፈጠራ ሥራዎች አዲስ ተነሳሽነትን ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
​#ethiopia #claude #anthropic #artificialintelligence #technews #digitalethiopia #ai #technology #addisababa #innovations

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.