3 months ago
አሜሪካ ክሎድን ለኢትዮጵያ ክፍት አደረገች
#ethiopia | የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር አዲስ የምስራች ተሰምቷል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ የማሰብ ብቃትና ውጤታማነቱ የሚታወቀውና በአሜሪካው አንትሮፒክ (Anthropic) ተቋም የሚበለጽገው ክሎድ (Claude) የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) አገልግሎት፣ ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ በይፋ ሥራ መጀመሩን አስታውቋል።
ይህ ትልቅ እመርታ እንዲመዘገብ የኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት ከአሜሪካው የምርምር ተቋም ጋር ሲያደርግ የነበረው ተከታታይና ውጤታማ የዲፕሎማሲ ውይይቶች ከፍተኛውን ሚና ተጫውተዋል።
ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የሚገኙ የቴክኖሎጂ አፍቃሪዎች፣ የሶፍትዌር አበልጻጊዎችና ተመራማሪዎች እነዚህን የላቁ የ-AI መሣሪያዎች በቀጥታ ለመጠቀም የነበረባቸውን ፈተና አሁን ላይ በይፋ ተፈቷል።
ኢትዮጵያ በአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ መካተቷ ተጠቃሚዎች የክሎድን የላቀ የኮዲንግ ብቃት፣ ጥልቅ የዳታ ትንተና እና ውስብስብ የምርምር ሥራዎችን በቀላሉ እንዲያከናውኑ ሰፊ የዕድል በር ከፍቶላቸዋል።
ይህም የሀገሪቱን የዲጂታል ምህዳር ከማሳደግ ባለፈ ለፈጠራ ሥራዎች አዲስ ተነሳሽነትን ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#ethiopia #claude #anthropic #artificialintelligence #technews #digitalethiopia #ai #technology #addisababa #innovations

7 months ago
🇸🇳 "ከአፍሪካ ዋንጫ ጋር ያለኝ ጉዞ አብቅቷል!" - ሳዲዮ ማኔ 👋
#ethiopia | ሜዳ ጥለው ሊወጡ ሲሉ ማኔ የወሰደው የጀግንነት እርምጃ እና የጡረታ ውሳኔው...
የሴኔጋሉ ኮከብ ሳዲዮ ማኔ ዋንጫውን ካነሳ በኋላ በሰጠው መግለጫ ሁለት ወሳኝ ጉዳዮችን አነሳ። አንደኛው ከአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ራሱን ማግለሉ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጨዋታው ተቋርጦ በነበረበት ሰዓት የተፈጠረውን ሁኔታ ነው።
🗣️ ሳዲዮ ማኔ ምን አለ?
1️⃣ ስለ ጡረታው:
"በመጀመሪያ የሴኔጋልን ህዝብ አመሰግናለሁ። ቀላል አልነበረም፤ ነገር ግን በጋራ አደረግነው። በጣም ደስተኛ ነኝ። ቀደም ብዬ እንደተናገርኩት፤ ለእኔ ከአፍሪካ ዋንጫ ጋር ያለኝ ነገር እዚህ ላይ አብቅቷል።" (በብሄራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎው የመጨረሻው መሆኑን አረጋግጧል)።
2️⃣ ስለ አወዛጋቢው ፔናልቲ እና ሜዳ ጥሎ ስለመውጣት:
"ፔናልቲውን በተመለከተ፣ እኔ ትክክለኛ ፔናልቲ ነበር ብዬ አላስብም። ነገር ግን ዳኛው ካለ ምንም ችግር የለም።"
"በወቅቱ ሁሉም ተጫዋች ሜዳውን ጥሎ መውጣት ፈልጎ ነበር። እኔ ግን ክሎድ ሊሮይን (Claude Le Roy) ምክር ጠየቅሁት፤ እሱም 'መጫወት አለባችሁ' አለኝ። ኤል ሀዲጂ ዲዩፍም (El Hadji Diouf) ተመሳሳይ ነገር ነገረኝ።"
"ከዚያም ለልጆቹ እንዲህ አልኳቸው፡- 'የሚመጣው ይምጣ እንጂ ኃላፊነት መውሰድ አለብን፤ እንገባለን እንጫወታለን!'"
ሳዲዮ ማኔ ሀገሩን በድል መርቶ በክብር ተሰናብቷል!
ቻው ጀግናው! 🦁👋
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#sadiomane #senegal #afcon2025 #legend #retirement #leadership #ethiopia

10 months ago
ኤአይ የፋይናንስን "ኤቨረስት" CFA ፈተናን በደቂቃዎች ውስጥ አለፈ
የዘመኑ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ያበለጸጓቸው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሞዴሎች፣ በዓለም የፋይናንስ ኢንዱስትሪ እጅግ ፈታኝ ተብሎ የሚታወቀውን የቻርተርድ ፋይናንሺያል አናሊስት (CFA) ፈተና ሦስቱን እርከኖች በሙሉ ማለፍ መቻላቸው ተገለጸ።
ይህ አስደናቂ ግኝት ይፋ የሆነው በአሜሪካው ኒው ዮርክ ዩኒቨርሲቲ (NYU) በተደረገ አዲስ ጥናት ነው። ጥናቱ OpenAI፣ Google (Gemini 2.5 Pro) እና Anthropic (Claude 4 Opus) የተባሉትን ከፍተኛ የኤአይ ሞዴሎች የፈተናውን ጥያቄዎች ለመመለስ ጥቂት ደቂቃዎችን ብቻ እንደወሰደባቸው አረጋግጧል።
ሦስተኛው እርከን ተሰናከለ
የCFA ፈተናን ለማለፍ የሰው ልጅ በተለምዶ ለዓመታት የተዘረጋ ≈1,000 ሰዓታት ጥናት ይፈልጋል። ሆኖም ኤአይዎች በተለይ የፋይናንስ ባለሙያዎችን የማመዛዘን እና የድርሰት (Essay) ችሎታ የሚፈትነውን "አስፈሪው" Level III ፈተናን በላቀ ውጤት ማለፋቸው ትልቅ ትኩረት ስቧል።
በ Level III ድርሰት ክፍል ላይ የኤአይ ሞዴሎች ያስመዘገቡት ውጤት (የማለፊያ ነጥብ 63% አካባቢ ነው):
የኤአይ ሞዴልየድርሰት ክፍል ውጤትOpenAI o4-mini79.1%Gemini 2.5 Pro75.9%Claude 4 Opus74.9%
ሚናው እየተቀየረ ነው
ይህ ውጤት በፋይናንስ ዓለም ውስጥ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቶችን አስፈላጊነት በተመለከተ ጥያቄዎችን ቢያጭርም፣ የኒው ዮርክ ተመራማሪዎች ግን ኤአይ ወዲያውኑ የCFA ቻርተር ባለቤት የሆኑ ሰዎችን ሚና አይተካም የሚል እምነት አላቸው።
ይልቁንም፣ የፋይናንስ ባለሙያዎች ትኩረታቸውን ወደማይተኩ የሰውነት ብቃቶች ማዞር እንዳለባቸው አሳስበዋል፦
የደንበኛ ግንኙነት እና አመኔታ መገንባት
የሥነ-ምግባር ብያኔና የኃላፊነት ስሜት
የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ውሳኔ አሰጣጥ
በገበያ ላይ የሚከሰቱ ያልተጠበቁ ለውጦችን በሰዎች አእምሮ መተርጎም
መደምደሚያው፦ ኤአይ የፋይናንስ ባለሙያዎችን ረዳት ይሆናል እንጂ ምትክ አይሆንም።
ነገር ግን፣ ይህ ግኝት የፋይናንስ የሥራ ባህሪ ከመሠረቱ እየተቀየረ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሲሆን፣ ለባለሙያዎችም ከእውቀት ክምችት ይልቅ በሰብዓዊ ብቃቶች ላይ እንዲያተኩሩ ማስጠንቀቂያ ሆኗል።
seledadotio

Sponsored by
Surafel
Comments