(ዘ-ሐበሻ ዜና) ኢትዮጵያና ኬንያን የሚያገናኘው መንገድ ተዘግቶ ዋለ፡፡ ኢትዮጵያንና ኬንያን የሚያገናኘው ከሶሎሎ እስከ ሞያሌ የተዘረጋው አውራጎዳና ዛሬ ዝግ ሆኖ ውሏል፡፡ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ተቃዋሚዎች መንገዱን በድንጋይና በተቃጠለ ጎማ መሙላታቸው ነው፡፡ የኬንያ ጋዜጦች እንደዘገቡት በሶሎሎ ውስጥ ዛሬ ከጠዋት አንስቶ ተቃዋሚዎች አደባባይ የወጡ ሲሆን በአካባቢው የሚኖሩ ሁለት ሽማግሌዎች መታገታቸውን ሲቃወሙ ውለዋል፡፡
እንደዘገባዎቹ አንደኛው የአካባቢው ሽማግሌ ትላንት ምሽት ፊታቸውን በጭንብል በሸፈኑ ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች የታገቱት ከመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ነበር፡፡ ሌላኛውን ደግሞ ወደናይሮቢ በመጓዝ ላይ እያሉ መኪናቸውን አስቁመው በሀይል ካስወረዷቸው በኋላ በሌላ መኪና ይዘዋቸው ሄደዋል፡፡ ተቃዋሚዎቹ በአካባቢያቸው ላይ ተደጋጋሚ እገታና የሰዎች መሰወር እየተፈፀመ የፀጥታ አካላት ይህንን ለማስቆም አለመቻላቸውን የገለፁ ሲሆን ለደህንነታቸው ስጋት እንዳደረባቸው ሲናገሩም ተደምጠዋል፡፡
በዚህ ተቃውሞ የተነሳ በኢትዮጵያና ኬንያ መካከል የሚደረገው የየብስ ግንኙነት ሊቋረጥ ችሏል፡፡ ይህ አውራ ጎዳና ሁለቱን አገራት በንግድ የሚያስተሳስራቸው በመሆኑ በርካታ የጭነት መኪናዎች በሁለቱም በኩል ረጅም ሰልፍ ቆመው ለመዋል ተገደዋል፡፡

3 months ago