Logo
Getu Temesgen
በኢራን የንግድ መርከብ ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተነገረ
#ethiopia | ​በስትራቴጂካዊው የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ በኢራን የባህር ኃይል እና በአሜሪካ የጦር መርከቦች መካከል የትጥቅ ግጭት መከሰቱን የኢራኑ ፋርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

​ትናንት ምሽት አሜሪካ በአንድ የኢራን የንግድ መርከብ ላይ በሰነዘረችው ጥቃት ሳቢያ በመርከቧ ላይ ከፍተኛ እሳት የተነሳ ሲሆን፣ በሰው ሕይወትና አካል ላይም ጉዳት ደርሷል።

​በጥቃቱ ሳቢያ በመርከቧ ላይ የነበሩ ሰራተኞች ላይ የደረሰው ጉዳት እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

​- 10 መርከበኞች የተለያዩ የመቁሰል አደጋዎች ደርሶባቸዋል።

​- መጀመሪያ ላይ 5 መርከበኞች የጠፉ ቢሆንም፣ የሚናብ ካውንቲ ገዥ መሐመድ ራድመህር እንደገለጹት ከሆነ የኦንዱ መርከበኛ አስከሬን ተገኝቷል።

​-አሁንም ደብዛቸው ያልታወቁ ቀሪ 4 መርከበኞችን ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

​ይህ በዓለም አቀፍ የንግድና የነዳጅ ዝውውር ቁልፍ በሆነው የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ላይ የተከሰተው ግጭት፣ በቀጠናው ያለውን ወታደራዊ ውጥረት ይበልጥ ሊያባብሰው እንደሚችል ተሰግቷል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ቅዳሜ_ገበያ

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.