Logo
Getu Temesgen
በአዲስ አበባ ከተማ ለአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ የቆመው የመታሰቢያ ሐውልት በይፋ ተመረቀ
#ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ አፍሪካ ፓርክ ውስጥ የተገነባው የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ ሐውልት በዛሬው ዕለት ተመርቋል።

የሐውልቱን የምረቃ ሥነ ሥርዓት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በይፋ የፈጸሙ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና ታዋቂ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት አርቲስቱ በኪነ ጥበብ ዘርፍ ለሀገሪቱ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እና ለሀገር ባለውለታነቱ ዕውቅና ለመስጠት በመዲናዋ ይህ የመታሰቢያ ሐውልት ሊቆምለት ችሏል።

ከንቲባዋ አክለውም ጥበብ ሀገርን የመገንባት አቅም እንዳላትና ሀገርም የጥበብ ሰዎችን ማክበር እንዳለባት በመግለጽ ጥበብ ሀገር ትሠራለች ሀገርም ጠቢብን ታከብራለች የሚለውን መልዕክት አስተላልፈዋል።
#ሀጫሉሁንዴሳ #መታሰቢያሐውልት #አዲስአበባ #ኪነጥበብ #ኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.