ከ2ሺህ 400 በላይ ሰዎች የዓይን ብሌን ለመለገስ ቃል ገቡ
በኢትዮጵያ የደምና ሕብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት ውስጥ 338 የዓይን ብሌን ለማሰባሰብ ታቅዶ 428 የዓይን ብሌን መሰብሰብ መቻሉን ተገልጿል።ህብረተሰቡን ቃል የማስገባት ስራ ላይ ሰፊ እንቅስቃሴ የተደረገ መሆኑን በኢትዮጵያ የደምና ሕብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ ገብረአብ ፍስሃ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት 2 ሺህ 410 ሰዎች ከህልፈታቸው በኋላ የዓይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለ270 ሰዎች ንቅለ ተከላ ዝግጁ ለማድረግ ታቅዶ በአጠቃላይ 313 የዓይን ብሌኖች በአዲስ አበባ እና በጅማ ለተለያዩ የሕክምና ተቋማት ተሰራጭቷል።ከነዚህም ውስጥ 173 ለመንግሥት ተቋማት፣ 134 ደግሞ ለግል ተቋማት ሆስፒታሎች እንዲሰራጭ ተደረጓል፡፡
አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ረጅም ዓመታት ያስቆጠረው የዓይን ባንክ እንደ ሀገር ተደራሽነቱ ውስን መሆኑ በተጨማሪም ህብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ ባለመኖሩ ቃል የሚገቡት ቁጥር አነሰተኛ መሆኑ የባንኩ ችግሮች ናቸው ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል፡፡የተሰበሰቡት የዓይን ብሌኖች ከአራቱ ተላላፊ በሽታዎች ነፃ መሆናቸው በላብራቶሪ ተረጋግጦ ንቅለ ተከላው እንደሚከናወን አቶገብረአብ ፍስሃ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
seledadotio

3 months ago