(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአለም የፕሬስ ነፃነት ኢንዴክስ ኢትዮጵያ 148ተኛ እንዲሁም ኤርትራ 180ኛ ደረጃን አገኙ፡፡ ሪፖርተርስ ዊዝአውት ቦርደርስ ወይንም አርኤስኤፍ የ2026 የአለም የፕሬስ ነፃነት ኢንዴክስን ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህ ኢንዴክስ ላይ እንደተገለፀው አለም ላይ ዘንድሮ የሁሉም አገራት የፕሬስ አያያዝ ዝቅተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
እንዲሁም ካለፉት 25 አመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ግማሽ ያህሉ የአለም አገራት ውስጥ የፕሬስ ነፃነት ‹‹አስቸጋሪ›› ወይንም ‹‹የከፋ›› ሆኖ መገኘቱን አስረድቷል፡፡ ይህንን ኢንዴክስ ለማውጣት እንደመስፈርትነት የተጠቀመው ለጋዜጠኞች ያለውን የኢኮኖሚ፣ የህግ፣ የደህንነት፣ የፖለቲካና የማህበራዊ ሁኔታዎች መሆኑን የገለፀው አርኤስኤፍ፣ ዘንድሮ አሜሪካ ደረጃዋ በ7 ደረጃዎች መውረዱን አስታውቋል፡፡ እንደኢንዴክሱ ከሆነ ኖርዌይ በዝርዝሩ ውስጥ ለጋዜጠኞች የተመቸች አገር በመሆን ዘንድሮ ለ10ረኛ ተከታታይ አመት በቀዳሚነት ተቀምጣለች፡፡
ኤርትራ ደግሞ ለ3ተኛ ተከታታይ አመት የመጨረሻው ረድፍ ላይ መገኘቷን አስታውቋል፡፡ የ180 አገራት ደረጃ በተቀመጠበት በዚህ ኢንዴክስ ጎረቤት አገር ኤርትራ በ180ኛ ቦታ ላይ ስትቀመጥ ከእሷ ከፍ ብላ በ179ነኛ ደረጃ ያለችው ሰሜን ኮሪያ ናት፡፡ 178ተኛ ላይ ደግሞ ቻይናን አስቀምጧል፡፡ እንዲሁም ኢራንን በ177ኛ ደረጃና ሩሲያን በ172ተኛ ደረጃ ላይ ያስቀመጠው ይህ ኢንዴክስ ለኢትዮጵያ ደግሞ የ148ተኛ ደረጃን ሰጥቷል፡፡ በኢንዴክሱ ላይ ኢትዮጵያ 4 ጋዜጠኞችን ላለፉት 3 አመታት የሽብርተኝነት ክስ መስርታ በእስር ላይ ማቆየቷንም አስታውቋል፡፡

3 months ago