Logo
Getu Temesgen
አዲሱ የአራዳ ፓርክ የታሪክ ማስታወሻ የውበት ምንጭና የዘመናዊነት መገለጫ
#ethiopia | የአራዳ ፓርክ ቀደም ሲል የነበረውን የቆሻሻ የብክለትና የድህነት ገጽታ ሙሉ በሙሉ በመቀየር በአዲስ መልክ የተገነባ ታላቅ ፕሮጀክት ነው::

ይህ ስራ የቆዩ አሉታዊ የታሪክ አሻራዎችን በማጥፋት የኢትዮጵያን አዲስ ማንነትና ውበት ለትውልድ በሚተርክ መልኩ ተከናውኗል::

ከፒያሳ አካባቢ የለቀቁ ነዋሪዎች ለሰብአዊ ክብር ከማይመጥኑ ቤቶች ወጥተው መሰረተ ልማት ወደተሟላላቸው ዘመናዊ መኖሪያዎች እንዲገቡ ተደርጓል::

ነዋሪዎቹ ማህበራዊ ትስስራቸውን ሳይበጥሱ እድርና እቁባቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ መደረጉም የልማቱ ልዩ ገጽታ ነው:: ፒያሳ ዳግም የተገነባችው እውነተኛ ስልጣኔን በሚያንጸባርቅ መልኩ ሲሆን በአካባቢው የነበሩ ወንዞችም ከቆሻሻ ጸድተው ለስራ እድል ፈጠራና ለቱሪስት መዳረሻነት እንዲውሉ ተደርገዋል::

በ40 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የአራዳ ፓርክ የሚከተሉትን ዋና ዋና አገልግሎቶች ይዟል

የመንገድና የትራንስፖርት መሰረተ ልማት

5 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ 6 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ 5 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መስመር እና 5 ኪሎ ሜትር የመሮጫ ትራክ ተገንብቶለታል::

የንግድና የፋይናንስ ዘርፍ

ከፒያሳ ለተነሱ ነጋዴዎች ቅድሚያ የሚሰጥባቸው 131 ዘመናዊ ሱቆች 7 ካፌና ሬስቶራንቶች አንድ ትልቅ ሱፐርማርኬት እና የባንክ ቅርንጫፍ ተካተዋል::

የመዝናኛና የስፖርት አገልግሎቶች

ዘመናዊ የአካል ብቃት ማእከል 7 አዳራሾች 8 ፕላዛዎች 3 አንፊ ቴአትሮች እና ማራኪ የሆነ ተንቀሳቃሽ ፏፏቴ ይገኛሉ:: በተጨማሪም 100 ሜትር ርዝመት ያለው የሀገሪቱ ረጅሙ የሰንደቅ ዓላማ መስቀያ በዚሁ ፓርክ ተተክሏል::

የህጻናትና ቤተሰብ ስፍራዎች

አራት ዘመናዊ የህጻናት መጫወቻዎች እና ህጻናት ስለ ሀገራቸው ግንዛቤ የሚያገኙበት ትንሿ ከተማ የተሰኘ ልዩ ስፍራ ተዘጋጅቷል::

የአረንጓዴ ልማትና የንጽህና አገልግሎት

15 ሄክታር መሬት በሳርና በተክሎች የተሸፈነ ሲሆን 22 የህዝብ መጸዳጃ ቤቶች እና 131 መኪናዎችን የሚይዝ ሰፊ ማቆሚያ ተገንብቷል::

ይህ ፕሮጀክት የመሬት አጠቃቀምን በብቃት ያረጋገጠ ሲሆን ከመሬት በታች ለሱቆችና ለአዳራሾች ከላይ ደግሞ ለፕላዛ አገልግሎት እንዲውል ተደርጓል::

እንዲሁም በአካባቢው የነበሩ ከ700 በላይ ታሪካዊ ቤቶችና ህንጻዎች ይዘታቸውን ሳይለቁ እንዲታደሱ ተደርጓል::

በአጠቃላይ ፓርኩ ከንግድ እስከ ስፖርት እንዲሁም ከቤተሰብ መዝናኛ እስከ ስነ ጥበብ መድረኮችን የያዘ የከተማዋ አዲስ የቱሪስት መስህብ ነው::
#aradapark #piassa #addisababacity #urbandevelopment #greenlegacy #tourismethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.