Logo
FastMereja
በድርድር የሚጭኑ የኤሌክትሮኒክስ ታክሲ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መጀመሩ ተገለጸ
#fastmereja I የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኤሌክትሮኒክስ ታክሲ (Ride) ስምሪት ወስደው ከሲስተም ውጪ በድርድር የሚጭኑ እና በህገወጥ ታሪፍ አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥርና እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታወቀ። እርምጃው በኮድ 3 የኤሌክትሮኒክስ ታክሲዎች እና በህገወጥ መንገድ በሚንቀሳቀሱ የኮድ 2 የቤት ተሽከርካሪዎች ላይ ያተኮረ ነው።

ቢሮው ባደረገው ክትትል፣ አንዳንድ አሽከርካሪዎች የድርጅት ሎጎ በመለጠፍ በተለይም ጠዋትና ማታ የሰው እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው አካባቢዎች ህገወጥ ተርሚናል በመፍጠር ያለ ሲስተም በጥሪና በግምት ታሪፍ ተሳፋሪዎችን ሲጭኑ ተገኝተዋል። ይህ አሰራር ከህጋዊው የኤሌክትሮኒክስ ታክሲ ስምሪት ውጪ መሆኑ ተገልጿል።

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.