Logo
Getu Temesgen
የጠፈርተኞቹ የሞት ሽረት ፍጥጫ
በሰላም ይመለሱ ይሆን?
#ethiopia | ​የሰው ልጅ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ ወደ ጨረቃ ያደረገው ታሪካዊ ጉዞ እጅግ አደገኛ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።

የአርቴሚስ 2 (Artemis II) አራቱ ጠፈርተኞች የ10 ቀናት የጨረቃ ዙሪያ ቆይታቸውን አጠናቅቀው ወደ ምድር አቅንተዋል።

​ከፍተኛ ስጋት የፈጠሩት ነጥቦች

​አስገራሚ ፍጥነት
መንኮራኩሯ በሰዓት 25,000 ማይል (ከድምፅ ፍጥነት በ30 እጥፍ በላይ) እየተምዘገዘገች ወደ ምድር ከባቢ አየር ትገባለች።

​ከፍተኛ ሙቀት
የመንኮራኩሯ ውጫዊ ክፍል እስከ 2,760 ዲግሪ ሴልሺየስ በሚደርስ እሳት ይፈተናል።

​የጋሻው ስንጥቅ ስጋት
በ2022ቱ የአርቴሚስ 1 ሙከራ ወቅት በመንኮራኩሯ የሙቀት መከላከያ ጋሻ ላይ ስንጥቆች ታይተው የነበረ ቢሆንም፣ አሁንም ጠፈርተኞቹ ያንኑ ተመሳሳይ ጋሻ መጠቀማቸው በባለሙያዎች ዘንድ ትልቅ ስጋት ፈጥሯል።

​ናሳ የመንኮራኩሯን አቅጣጫ በመቀየር አደጋውን ለመቀነስ እንደሚቻል ገልጾ ሙሉ በራስ መተማመን አሳይቷል። በአሁኑ ወቅት በሳንዲያጎ የባሕር ዳርቻ የነፍስ አድን መርከቦችና የሕክምና ቡድኖች በጉጉት እየጠበቁ ይገኛሉ።

​የዚህ ተልዕኮ ስኬት የሰው ልጅን በድጋሚ ጨረቃ ላይ ለማሳረፍ ለታቀደው የአርቴሚስ 3 ፕሮጀክት ብቸኛው መሠረት ነው!

​#getu #artemis2 #nasa #spaceexploration #moonmission #reentry #sciencenews #astronauts #spacex #addisababa #ጠፈር #አርቴሚስ #ናሳ #ጨረቃ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.