3 months ago
አሜሪካ ከጨረቃ በኋላ ቀጣዩ ግቧ ማርስ ነው - ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ
*****************
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአርቴሚስ 2 ተልዕኮ የጠፈርተኞች አባላትን በኋይት ሀውስ ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት፣ ከጨረቃ በኋላ ቀጣዩ ግቧችን ማርስ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በኋይት ሀውስ በተካሄደው በዚህ የዕውቅና ሥነ-ሥርዓት ላይ አራቱም የአርቴሚስ 2 ተልዕኮ አባላት የተገኙ ሲሆን፣ ፕሬዝዳንቱ ለጠፈርተኞቹ ያላቸውን ከፍተኛ አድናቆት ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለጠፈርተኞቹ ባስተላለፉት መልዕክት፤ "እናንተ የአሜሪካ እውነተኛ ጀግኖች ናችሁ" በማለት፣ ጉዟቸው የሀገሪቱን ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለምን ትኩረት የሳበና የማይታመን ጀግንነት የታየበት መሆኑን ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሜሪካ በጠፈር ምርምር ያላትን መሪነት በድጋሚ ለማረጋገጥ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸው፣ በቀጣይ ጠፈርተኞችን በጨረቃ ላይ ለማሳረፍ ያለውን እቅድ አረጋግጠዋል።
"በዚህ ጊዜ ባንዲራችንን የምንተክለው ለጥቂት ጊዜ ቆይተን ለመመለስ ሳይሆን በጨረቃ ላይ ቋሚ መገኛ እንዲኖረንና ከዚያም ወደ ማርስ ለመሻገር ነው" ሲሉ የሀገራቸውን የረጅም ጊዜ የጠፈር ፍላጎት አስረድተዋል።
የአርቴሚስ 2 ጠፈርተኞች በዚህ ጉዞ እስካሁን ማንኛውም የሰው ልጅ ተጉዞ ከማያውቀው ርቀት በላይ ለ10 ቀናት ከምድር ርቀው በመጓዝ አዲስ ታሪክ ያስመዘገቡ ሲሆን፤ በጉዞው የተሰበሰበው መረጃም የሰውን ልጅ ወደ ጨረቃ ደቡባዊ ዋልታ ለሚወስደው የአርቴሚስ 3 ተልዕኮ እንደግብዓት እንደሚያገለግል ተገልጿል።
በቢታንያ ሲሳይ
#ethiopianbroadcastingcorporation #usa #artemisii #donaldtrump #spaceexploration #nasa

4 months ago
የጨረቃ ተጓዦች በሰላም ምድር ደረሱ!
#ethiopia | የሰው ልጅ በጠፈር ምርምር ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተው የናሳው **አርቴሚስ II (Artemis II) ተልዕኮ በታላቅ ስኬት ተጠናቋል። አራት ጠፈርተኞችን ያሳፈረችው የኦራይን (Orion) መንኩራኩር፣ ጨረቃን ዙራ ካደረገችው አስደናቂ ቆይታ በኋላ አርብ ምሽት በፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ በሰላም አርፋለች።
የዚህን ታሪካዊ ጉዞ ዋና ዋና ኩነቶች እነሆ፦
በምስራቅ አቆጣጠር ከምሽቱ 8 ሰዓት ገደማ መንኩራኩሯ ውቅያኖስ ላይ ስታርፍ፣ የአንድ ዓመት ዝግጅትና የሰባት ቀናት የጠፈር ቆይታ በድል ተደምድሟል።
ተጓዦቹ የሰው ልጅ ከዚህ ቀደም ደርሶበት የማያውቀውን ጥልቅ ህዋ በማሰስ እና ከምድር በጣም ርቆ በመጓዝ አዲስ የዓለም ሪከርድ ማስመዝገብ ችለዋል።
የዚህ ተልዕኮ ስኬት ናሳ የሰው ልጅን በድጋሚ በጨረቃ ላይ ለማሳረፍ ለሚጠብቀው አርቴሚስ III ተልዕኮ ትልቅ መተማመንን የፈጠረ ሲሆን፣ ወደ ማርስ ለሚደረገው ጉዞም እንደ ትልቅ መነሻ ተወስዷል።
በአሁኑ ወቅት አራቱ ጀግና ጠፈርተኞች በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ አስፈላጊው የሕክምና ክትትል ተደርጎላቸው ወደ ቤተሰቦቻቸው በመመለስ ላይ ናቸው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #artemisii #nasa #spaceexploration #orion #moonmission #technews #science #የጠፈር_ምርምር #አርቴሚስ2 #ናሳ

የጠፈርተኞቹ የሞት ሽረት ፍጥጫ
በሰላም ይመለሱ ይሆን?
#ethiopia | የሰው ልጅ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ ወደ ጨረቃ ያደረገው ታሪካዊ ጉዞ እጅግ አደገኛ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።
የአርቴሚስ 2 (Artemis II) አራቱ ጠፈርተኞች የ10 ቀናት የጨረቃ ዙሪያ ቆይታቸውን አጠናቅቀው ወደ ምድር አቅንተዋል።
ከፍተኛ ስጋት የፈጠሩት ነጥቦች
አስገራሚ ፍጥነት
መንኮራኩሯ በሰዓት 25,000 ማይል (ከድምፅ ፍጥነት በ30 እጥፍ በላይ) እየተምዘገዘገች ወደ ምድር ከባቢ አየር ትገባለች።
ከፍተኛ ሙቀት
የመንኮራኩሯ ውጫዊ ክፍል እስከ 2,760 ዲግሪ ሴልሺየስ በሚደርስ እሳት ይፈተናል።
የጋሻው ስንጥቅ ስጋት
በ2022ቱ የአርቴሚስ 1 ሙከራ ወቅት በመንኮራኩሯ የሙቀት መከላከያ ጋሻ ላይ ስንጥቆች ታይተው የነበረ ቢሆንም፣ አሁንም ጠፈርተኞቹ ያንኑ ተመሳሳይ ጋሻ መጠቀማቸው በባለሙያዎች ዘንድ ትልቅ ስጋት ፈጥሯል።
ናሳ የመንኮራኩሯን አቅጣጫ በመቀየር አደጋውን ለመቀነስ እንደሚቻል ገልጾ ሙሉ በራስ መተማመን አሳይቷል። በአሁኑ ወቅት በሳንዲያጎ የባሕር ዳርቻ የነፍስ አድን መርከቦችና የሕክምና ቡድኖች በጉጉት እየጠበቁ ይገኛሉ።
የዚህ ተልዕኮ ስኬት የሰው ልጅን በድጋሚ ጨረቃ ላይ ለማሳረፍ ለታቀደው የአርቴሚስ 3 ፕሮጀክት ብቸኛው መሠረት ነው!
#getu #artemis2 #nasa #spaceexploration #moonmission #reentry #sciencenews #astronauts #spacex #addisababa #ጠፈር #አርቴሚስ #ናሳ #ጨረቃ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

ምድር ፎቶ ተነሳች
#ethiopia | ናሳ ለአርጤምስ 2 (Artemis II) ተልዕኮ ወደ ጨረቃ የላካቸው አራት ጠፈርተኞች፣ ከምድር 66,000 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሆነው የቀረጿቸውን እጅግ አስደናቂ እና ጥራት ያላቸውን የምድራችን ምስሎች ይፋ አድርገዋል።
እነዚህ ታሪካዊ ምስሎች የተነሱት የኦርዮን (Orion) መንኮራኩር ወደ ጨረቃ የምታደርገውን ጉዞ በጀመረችበት ወቅት ሲሆን፣ ይህም የሰው ልጅ በ1972 ከተካሄደው የአፖሎ 17 ጉዞ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከምድር ምህዋር ወጥቶ ወደ ጥልቅ ጠፈር የተጓዘበት አጋጣሚ ሆኖ ተመዝግቧል።
ይህ ተልዕኮ በበርካታ ምክንያቶች ታሪካዊና ልዩ ተደርጎ ተወስዷል፦
ተልዕኮው ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት እና ጥቁር አሜሪካዊ ጠፈርተኞችን በማካተት የጠፈር ምርምር ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል።
የአርጤምስ 2 ስኬት የሰው ልጅን ዳግም በጨረቃ ላይ ለማሳረፍ ለሚታቀደው የ"አርጤምስ 3" ተልዕኮ ወሳኝ መሠረት የሚጥል ነው።
መንኮራኩሯ ከላከቻቸው ምስሎች ጥራት መረዳት እንደሚቻለው፣ የናሳ የቴክኖሎጂ አቅም ለጥልቅ ህዋ ምርምር ዝግጁ መሆኑን አመላካች ነው።
የአርጤምስ 2 ተልዕኮ የሰው ልጅ የጨረቃን ምህዋር ዙሮ ወደ ምድር በመመለስ፣ ለወደፊቱ የሰው ልጅ የጨረቃና የማርስ ጉዞዎች መንገዱን ክፍት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#tikvah #getutemesgen #getu #nasa #artemisii #spaceexploration #earthfromspace #moonmission #sciencenews #techethiopia #spacetravel

7 months ago
🌒 ስምዎ ጨረቃን ዞሮ እንዲመጣ ከፈለጉ ፤ ናሳ ግብዣ አቅርቧል! 🚀
#ethiopia | የአሜሪካው የህዋ ምርምር ተቋም (NASA) እና የካናዳ የህዋ ኤጀንሲ በመተባበር፣ Artemis-II በተሰኘው ታሪካዊ ሚሽን ስምዎን ወደ ጨረቃ የመላክ ድንቅ አጋጣሚ ፈጥረዋል።
👨🚀 ስለ በረራው ምን ይታወቃል?
* ተልዕኮው፦ 4 አስትሮኖመሮችን በኦሪዮን (Orion) መንኮራኩር ጭኖ ጨረቃን በማዞር ወደ ማርስ ለሚደረገው የወደፊት ጉዞ ዝግጅት ማድረግ ነው።
* ርቀቱ፦ መንኮራኩሯ ከጨረቃ ወለል በላይ ከ4,600 እስከ 7,000 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትዞራለች
* ቆይታው፦ ለ10 ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ በኤፕሪል 2026 ከፍሎሪዳ ተነስቶ በፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ ያርፋል።
✍️ ስምዎን እንዴት መላክ ይችላሉ?
ናሳ ማንኛውም ሰው ስሙን በዲጂታል መልክ እንዲያስመዘግብ ጋብዟል።
* ስምዎ በትንሽ SD Card ላይ ተጭኖ በመንኮራኩሯ ውስጥ ይቀመጣል።
* ምዝገባውን ሲያጠናቅቁ የጉዞ ዝርዝርዎን የያዘ ዲጂታል የበረራ መሳፈሪያ (Boarding Pass) ይሰጥዎታል።
* ማሳሰቢያ፦ ስም ማስመዝገቢያው የሚያበቃው እስከ January 22, 2026 ድረስ ብቻ ነው።
ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ ለመጠቀም እና ስምዎን ከዋክብት መካከል ለማሳረፍ ከታች ባለው ሊንክ ይመዝገቡ፦
👉 https://www3.nasa.gov/send-your-name-with-artemis/
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#nasa #artemis2 #moonmission #spacescience #orion #astronomy #ethiopia #technews #spaceexploration

Comments