''ሊባኖስ ገና ቅጣቷን አልጨረሰችም'' ኔታንያሁ
#ethiopia | በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት አዲስ መልክ እየያዘ ባለበት በዚህ ወቅት፣ እስራኤል ሌሊቱን ይፋ የተደረገውን ባለ ሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት እንደምትደግፍ አስታውቃለች። ይሁን እንጂ ይህ ስምምነት "ሊባኖስን እንደማያካትት" ግልጽ በማድረግ ጉዳዩን ወደ ሌላ አቅጣጫ መልሳዋለች።
የጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ፣ በኢራን እና በምዕራባውያን መካከል የተደረሰውን ስምምነት መቀበሏን አረጋግጧል።
እንደ እስራኤል መግለጫ ከሆነ፣ ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት የሚቆየው ይሄው ስምምነት የሚከተሉትን ዋና ዋና ጉዳዮች ይዟል፦
እስራኤል በኢራን ላይ የምታደርሰውን ወታደራዊ እርምጃ ታቆማለች።
ኢራን ወሳኝ የሆነውን የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ለትራንስፖርት ክፍት ታደርጋለች።
ኢራን በአሜሪካ፣ በእስራኤል እና በቀጠናው አገራት ላይ የምታደርሰውን ማንኛውንም ጥቃት ለሁለት ሳምንታት ሙሉ በሙሉ ታቆማለች።
አሜሪካ ኢራን "የኑክሌር፣ የሚሳኤል እና የሽብር ስጋት እንዳትሆን" የምታደርገውን ጥረት እስራኤል እንደምትደግፍ ገልጻለች።
የዚህ ስምምነት ትልቁ አነጋጋሪ ነጥብ በሊባኖስ በኩል ያለው ግንኙነት ነው። የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼህባዝ ሻሪፍ ስምምነቱ ሊባኖስንም እንደሚያካትት ቀደም ብለው ቢናገሩም፣ የእስራኤል ወገን ግን ይህንን በፍጹም ውድቅ አድርጎታል።
"ይህ ስምምነት ሊባኖስን አያካትትም" ሲል የኔታንያሁ ቢሮ በግልጽ አስታውቋል።
ይህም ማለት እስራኤል ከኢራን ጋር "ጊዜያዊ ሰላም" ብታወርድም፣ በሰሜን በኩል ከሂዝቦላህ ጋር የምታደርገው ፍልሚያ እንደማይቆም ፍንጭ ሰጥታለች። ቀጠናው ለሁለት ሳምንታት "እፎይ" ቢልም፣ የሊባኖስ ሰማይ ግን አሁንም በስጋት እንደተሸፈነ ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #israel #iran #ceasefire #lebanon #middleeastnews #breakingnews

2 months ago