የ73ኛው ሚስ ወርልድ ተሳታፊን ለመለየት የሚደረገው የ"ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ" የመጨረሻ ውድድር ሚያዝያ 14 ይካሄዳል
#fastmereja I አዲስ አበባ
በቬትናም በሚካሄደው 73ኛው ዓለም አቀፍ የሚስ ወርልድ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክላ የምትሳተፈውን ቆንጆ ለመለየት የሚደረገው የ"ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ 2026" የመጨረሻ ውድድር፣ በመጪው ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. በካፒታል ሆቴል እንደሚካሄድ ተነገረ።
በናሽናል ዳይሬክተሯ ሞዴል ገነት ፀጋዬ የሚመራው "ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ ቢዩቲ ፓጀንት" የመጀመሪያ ዙር የምልመላ መርሃ-ግብሩን መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም. በኩሪፍቱ ሪዞርት አፍሪካን ቪሌጅ አካሂዷል። በዚህ የምልመላ ሂደት ላይ ከ80 በላይ ተወዳዳሪዎች የቀረቡ ሲሆን፣ ለፍፃሜው የሚያልፉ ምርጥ 40 ቆነጃጅት በዳኞች መመረጣቸው ታውቋል።
ለ23 ዓመታት በዘርፉ የቆየው ድርጅቱ፣ አሸናፊዋን ሙሉ ወጪዋን በመሸፈን በዓለም አቀፉ መድረክ ላይ ሀገሯን እንድታስተዋውቅ ያደርጋል። ለዘንድሮው ውድድር ስኬታማነት የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን፣ የባህልና ኪነ-ጥበብ ቢሮ፣ ኩሪፍቱ ሪዞርት እንዲሁም የተለያዩ የሙያ አጋሮች ድጋፍ እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል።
ከ130 በላይ ሀገራት የሚሳተፉበትና ከሁለት ቢሊዮን በላይ ተመልካቾች በቀጥታ ስርጭት የሚከታተሉት "ሚስ ወርልድ" በዓለም ላይ ካሉ የቁንጅና ውድድሮች ቀዳሚውና አንጋፋው እንደሆነ ይታወቃል።

4 months ago