Logo
FastMereja
በአለታ ወንዶ የንግድ ባንክ አገልግሎት መቆራረጥ በንግዱ ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ እሮሮ ቀሰቀሰ
#fastmereja I በአለታ ወንዶ ከተማ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በየቀኑ በሚያጋጥሙ የ"ሲስተም" እና የ"መብራት" መቆራረጦች ሳቢያ ደንበኞች ለአላስፈላጊ እንግልትና ለኢኮኖሚ ኪሳራ እየተዳረጉ መሆኑ ተገለጸ።

በሲዳማ ክልል የንግድ እንቅስቃሴ ማዕከልና የቡና ምርት መውጫ በሆነችው አለታ ወንዶ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎት አሰጣጥ ከከተማዋ የንግድ ፍሰት ጋር አለመመጣጠኑ ተገልጋዮችን እያስመረረ ይገኛል። ባንኩ "መብራት የለም" እና "ኔትወርክ ተቋርጧል" በሚሉ ምክንያቶች ስራ የሚያቆምባቸው ሰዓታት መብዛታቸው፣ በከተማዋ ያለውን የገንዘብ ዝውውር ሽባ እያደረገው መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ጉዳዩን አስመልክቶ ያነጋገርናቸው የንግዱ ማህበረሰብ አባላት እንደገለጹት፣ ባንኩ እንደ አማራጭ ሊጠቀማቸው የሚገቡ የጄነሬተርና የሳተላይት ኢንተርኔት አገልግሎቶች አለመኖራቸው ለችግሩ መባባስ ዋነኛ ምክንያት ነው። ይህ መጉላላት በደንበኞችና በባንኩ መካከል ያለውን የ"አገልግሎት ደረጃ ውል" የሚጥስ ከመሆኑም ባለፈ፣ በብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት የፋይናንስ ተቋማት ሊያሟሏቸው የሚገቡ ዝቅተኛ የአገልግሎት መስፈርቶችን ያላሟላ መሆኑን ይጠቅሳሉ።

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.