Logo
Getu Temesgen
ከ600 ሺህ በላይ ተማሪዎችን የሚያሳትፈው "የስፔሊንግ ቢ" ውድድር ይፋ ሆነ! ✨
#ethiopia | ​የኢትዮጵያ ስፔሊንግ ቢ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር በመሆን በመዲናችን በሚገኙ የመንግሥትና የግል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ከ600,000 በላይ ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ታሪካዊ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

​ተማሪዎች ከመደበኛው ትምህርት ጎን ለጎን የቃላት ዕውቀታቸውንና የማንበብ ባህላቸውን እንዲያሳድጉ ማስቻል።

​ በውድድሮች ላይ በመሳተፍ ተማሪዎች በራስ መተማመናቸውንና የመግባባት ብቃታቸውን እንዲገነቡ ማድረግ።

​ለነገው ዓለም ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን ለማፍራት የሚያስችል መድረክ መፍጠር።

የኢትዮጵያ ስፔሊንግ ቢ መስራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ አብይ ተክሌ እንደገለጹት፣ ይህ ስምምነት ለልጆች የተገባ ትልቅ ቃል ኪዳን ነው። የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮም ፕሮግራሙ ስኬታማ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጧል።

​በቅርቡ በትምህርት ቤቶች ደረጃ በሚጀመሩት የቃላት ዝርዝር እንቅስቃሴዎችና ውድድሮች ተማሪዎች በንቃት እንዲሳተፉ ይጠበቃል።

​#getu #ethiopiaspellingbee #educationaddis #spellingbeeethiopia #studentexcellence #addisababaeducation #futureleaders #literacymatters #የስፔሊንግቢ #ትምህርት #አዲስአበባ #ንባብ #ተማሪዎች #ጌጡተመስገን #getutemesgen

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.