Logo
Getu Temesgen
''የአፍሪካ ዋንጫ ባለቤት ሞሮኮ በመሆኗ ደስ ብሎኛል'' አሽራፍ ሀኪሚ
#ethiopia | ሴኔጋል በሜዳ ላይ አሸንፋ የነበረ ቢሆንም፣ የካፍ (CAF) ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ በወሰነው ያልተጠበቀ ውሳኔ፣ ውጤቱን በመሻር ዋንጫውን በፎርፌ ለሞሮኮ መስጠቱ አይዘነጋም።

አሁን ደግሞ የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን አምበል አሽራፍ ሀኪሚ ዝምታውን ሰብሯል። ሀኪሚ ይህን የካፍ ውሳኔ እና የዋንጫ ድል በታላቅ ደስታ እንደሚቀበለው በይፋ ገልጿል።

“የአፍሪካ ዋንጫውን በዚህ መንገድ (በፎርፌ) ማሸነፍ ቢኖርብንም፣ በታላቅ ደስታ እንቀበለዋለን፤” ሲል አምበሉ ሀኪሚ ተናግሯል። አክሎም “በድሉ እጅግ በጣም ደስተኞች ነን፤ ይህንን ጊዜም ለረጅም ጊዜ ስጠብቀው ነበር” በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል።

እርግጥ ነው፣ ነገሮች ገና እልባት አላገኙም! የካፍ የመጨረሻ ውሳኔ አሁን በዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት (TAS) ውሳኔ እንዲሰጥበት ተላልፏል። የሴኔጋል ይግባኝ ውጤቱን ሊቀለብሰው ይችላል ወይስ ሞሮኮ ዋንጫዋን በይፋ ታስቀራለች? በቀጣይ አዳዲስ መረጃዎች ሲወጡ የምናቀርብላችሁ ይሆናል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #afcon #hakimi #morocco #senegal #caf #tas #footballnews #abelbirhanu #ethiopiannews #sportupdates

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.