በቀይ ባሕር ላይ ውጥረት ነግሷል
#ethiopia | የብሉምበርግ ዘገባ የዜና ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ እንደገለጸው፣ ኢራን በየመን የሚገኙት የሁቲ አማፂያን በንግድ መርከቦች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲቀጥሉ ግፊት እያደረገች ነው።
ይህ የኢራን ፍላጎት የመነጨው አሜሪካ በኢራን ላይ የምታደርገውን ወታደራዊ ጫና ለመቀልበስና በንግድ መስመሩ ላይ መስተጓጎል በመፍጠር አጸፋዊ ተፅዕኖ ለማሳረፍ ካለ እቅድ መሆኑ ተመላክቷል።
በሁቲዎች መካከል ያለው የሐሳብ ልዩነት
ምንም እንኳን ሁቲዎች በቅርቡ ወደ እስራኤል በቀጥታ ሚሳኤሎችን በመተኮስ ግጭቱ ውስጥ ቢገቡም፣ በቀይ ባሕር ላይ የሚደረገውን የባሕር ላይ ጥቃት በድጋሚ ስለመጀመር ግን በቡድኑ አመራሮች መካከል መከፋፈል መኖሩ ተገልጿል።
ከዚህ ቀደም በጋዛ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ለማስቆም በሚል በንግድ መርከቦች ላይ የተሰነዘሩ ጥቃቶች በዓለም አቀፍ የንግድ ፍሰት ላይ ከፍተኛ ቀውስ አስከትሎ እንደነበር ይታወሳል። አሁን የተጀመረው አዲስ እንቅስቃሴ ቀጠናውን ወደ ከፋ የጸጥታ ስጋት ሊከተው እንደሚችል ተሰግቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #redsea #breakingnews #middleeastconflict #houthi #iran #internationaltrade #maritimesecurity

6 months ago