Logo
FastMereja
በአዲስ አበባ የህፃናት የአፈጣጠር ችግር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ !
#fastmereja I የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከማያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር በአፈጣጠር ችግር ምክንያት በሚከሰቱ የጀርባ አጥንት ክፍተት (Spina Bifida) እና የአንጎል ውስጥ ፈሳሽ መከማቸት (Hydrocephalus) ህመሞች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ-ግብር አካሂዷል።

በኢትዮጵያ በአመት ከ44 ሺህ በላይ ህፃናት በእነዚህ የጤና ችግሮች ምክንያት እንደሚወለዱ የተገለጸ ሲሆን፣ ለችግሩ ዋነኛው መንስኤ የእናቶች የፎሊክ አሲድ (ቫይታሚን ቢ9) እጥረት መሆኑ ተገልጿል።

እነዚህ ህፃናት በአፈጣጠር ችግሩ ሳቢያ ለዕድሜ ልክ የመንቀሳቀስ መገደብ እና ራስን ችሎ የመፀዳዳት ችግር እንደሚገጥማቸውም ተመላክቷል።

ችግሩን በዘላቂነት ለመከላከል በመንግስት የተጀመረው በፎሊክ አሲድ ወይም በቫይታሚን ቢ9 የበለፀጉ ምግቦችን ለህብረተሰቡ የማቅረብ (Food Fortification) ስራ ያለውን ፋይዳ ማሳደግ እንደሚገባ ተገልጿል።

የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩም ይህንን ሀገራዊ ጥረት በግለሰብ፣ በማህበረሰብ እና በሀገርአቀፍ ደረጃ ለማገዝ ያለመ እንደሆነ ተጠቁሟል።

የአካቶ ትምህርት እና ተጠቃሚነት ከመከላከል ስራው ባሻገር፣ በእነዚህ የጤና ችግሮች የተጠቁ ህፃናት የማህበረሰቡ አካል መሆናቸው ታምኖበት፣ የአካቶ ትምህርት (Inclusive Education) ተጠቃሚ የመሆን መብታቸው ሊከበር እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል፡፡

መድረኩም በእነዚህ ህፃናት ሰብአዊ መብት እና ማህበራዊ ተሳትፎ ዙሪያ ሰፊ ውይይትም አካሂዷል።

በዛሬዉ መርሀ-ግብር የጤና ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎች፣የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አመራሮች፣የጥበብ ባለሙያዎች እና የሚዲያ አካላት፣ እንዲሁም የችግሩ ተጋላጭ የሆኑ ህፃናትና ወላጆቻቸው ተገኝተዋል

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.