አዎ! ቲቢን ለማጥፋት እንችላለን! ...
#ethiopia | የጤና ሚኒስቴር 20ኛውን ዓመታዊ የቲቢ ምርምር ጉባኤ እና የዓለም አቀፍ የቲቢ ቀንን ምክንያት በማድረግ ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ያዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተካሂዷል።
ይህ የንቅናቄ መድረክ የተዘጋጀው የሚዲያ አካላት በበሽታው መከላከል እና መቆጣጠር ስራ ላይ ያላቸውን ከፍተኛ ሚና ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲወጡ ለማስቻል ሲሆን በስልጠናው ላይ ከተለያዩ ተቋማት የተወከሉ የጤና ባለሙያዎች እና ጋዜጠኞች ተሳትፈዋል።
በውይይቱ ላይ የተገኙት የአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ፤ በሽታውን ከመከላከል ባለፈ ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ህብረተሰቡን በማንቃት በኩል የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
በጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሕይወት ሰለሞን በበኩላቸው፤ የሚዲያ ባለሙያዎች ስለ በሽታው ትክክለኛ መረጃ ለህዝብ በማድረስ ረገድ ያላቸውን ፋይዳ አብራርተዋል።
በጤና ሚኒስቴር የቲቢ፣ ስጋ ደዌ እና ሌሎች የሳንባ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ዴስክ ኃላፊ አቶ ታየ ለታ ደግሞ፤ የቲቢ በሽታ ዛሬም በሰው ዘር ላይ ከፍተኛ ሕመምና ሞት እያስከተለ መሆኑን በመጠቆም፣ ቁጥጥሩን ለማጠናከር ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የዓለም ቲቢ ቀን በየዓመቱ መጋቢት 15 ቀን (March 24) የሚከበር ሲሆን፣ ዕለቱ የተመረጠውም የዛሬ 140 ዓመት ታዋቂው ጀርመናዊ ተመራማሪ ዶ/ር ሮበርት ኮች የቲቢ በሽታ መንስኤ የሆነውን “ማይኮባክቴሪያም ቲዩበርክሎስስ” ማግኘቱን ለዓለም ያበሰረበትን ቀን ለማስታወስ ነው።
ዘንድሮም ቀኑ “አዎ! ቲቢን ለማጥፋት እንችላለን! በመንግስት መሪነት፤ በሕዝባችን ኃይል!!” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ይከበራል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#ethiopia #health #worldtbday #tbprevention #mediaawareness #publichealth #getutemesgen

3 months ago