ሉካሼንኮ ለኪም ጆንግ ኡን የጦር መሳሪያ በስጦታ አበረከቱ
የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ በሰሜን ኮሪያ ፒዮንግያንግ ባደረጉት ጉብኝት ለሀገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን አውቶማቲክ ጠመንጃ በስጦታ አበረከቱ።
ሉካሼንኮ ስጦታውን ሲያስረክቡ "ጠላቶች ቢመጡ ትጠቀምበታለህ" በማለት በቀልድ መልክ መናገራቸው ተዘግቧል። ኪም ጆንግ ኡንም በምላሹ የራሳቸው ምስል ያለበትና ከባህር ዛጎል የተሰራ ትልቅ የአበባ ማስቀመጫ ሰጥተዋል።
ሁለቱ መሪዎች በምዕራባውያን ላይ ያላቸውን ተቃውሞ በመግለጽ የ"ወዳጅነትና ትብብር" ስምምነት ተፈራርመዋል።
ቤላሩስና ሰሜን ኮሪያ በዩክሬን ጦርነት ሩሲያን በግልጽ የሚደግፉ ሲሆን፣ ጉብኝታቸውም አዲስ የትብብር ምዕራፍ መክፈቻ መሆኑ ተገልጿል።
ስምምነቱ ከግብርና እስከ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ያሉ ዘርፎችን ያጠቃልላል።
ምንጭ፦ AFP

5 months ago