የኢትዮጵያን እወነተኛ ገጽታ ለዓለም ለማስተዋወቅ ኢንፍሉዌንሰር ቱር ኢትዮጵያ 2026 ይፋ ሆነ!
#fastmereja :የኢትዮጵያን ተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊና ባህላዊ እሴቶች ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይበልጥ ለማስተዋወቅ ያለመ ''ኢንፍሉዌንሰር ቱርኢትዮጵያ 2026" የተሰኘ ግዙፍ የዲጂታል ዘመቻ ትናንት በይፋ ተጀመረ፡፡
በኤን ዜድ ኮሙኒኬሽን (NZ Communications) አማካኝነት የተዘጋጀው ይህ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ንቅናቄ፣ ታዋቂ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎችንና ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን (Influencers) በማስተባበር የኢትዮጵያን ትክክለኛ ገጽታ በተቀናጀ መልኩ እንዲያስተዋውቁ ለማድረግ የታለመ መሆኑ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተገልጿል።
ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በሦስት ታዋቂ የዲጂታል አምባሳደሮች የሚመራ ሲሆን፣ እነሱም ብሩክ ኒውስ (Brook News)፣ ብሩክ ዚቲ (Bruck Zitty) እና ዮሐንስ ተሾመ ናቸው፡፡
እነዚህ ግለሰቦች ያላቸውን ሰፊ ተከታይና የዲጂታል ክህሎት በመጠቀም፣ በኢትዮጵያ ዙሪያ የሚሰሩ ይዘቶች ከፍተኛ መነቃቃትን እንዲፈጥሩና የማህበረሰብ ተሳትፎን እንዲያሳድጉ ይጠበቃል።
የዘመቻው አዘጋጅ ኤን ዜድ ኮሙኒኬሽንስ እንደገለጸው፣ ንቅናቄው ከመደበኛው የማስታወቂያ አቀራረብ ይልቅ በሰዎች መካከል በሚፈጠር ቀጥተኛ ግንኙነትና በእውነተኛ የልምድ ልውውጥ (Digital Storytelling) ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ልዩ እንደሚያረገዉ ተገልጿል።
በፕሮጀክቱ ላይ የሚሳተፉ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የሀገሪቱን ባህልና ማንነት ያለ ምንም ክፍያ በፈቃደኝነት የሚያስተዋውቁ ሲሆን፣ ይህም ለሀገራዊ ኩራትና ለዓለም አቀፍ ታዋቂነት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተጠቁሟል።
ይህ ተነሳሽነት ታዋቂ ኢትዮጵያውያን ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን በአንድ ላይ በማሰባሰብ በየክልሉ እንዲጓዙና ከማህበረሰቡ ጋርእንዲገናኙ በማድረግ፣ የኢትዮጵያን የአኗኗር ዘይቤና ያሉትን የኢንቨስትመንት ዕድሎች ለዓለም አቀፍ ታዳሚዎች ተደራሽ ለማድረግ አልሟል።
በተጨማሪም ንቅናቄው ለግል ድርጅቶችና ብራንዶች የኢትዮጵያን ገጽታ በመገንባቱ ሂደት ውስጥ አጋር በመሆን የድርጅታቸውን ተደራሽነት እንዲያሰፉ ዕድል እንደሚሰጥም ተገልጿል።

5 months ago