በካቻ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ላይ ተጥሎ የነበረው የባንክ እግድ በከፊል ተነሳ
የፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ፣ በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዐቃቤ ህግ ባቀረበው አቤቱታ መሰረት በካቻ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ (Kacha Financial Technology) ላይ ተጥሎ የነበረው የባንክ እግድ እንዲሻሻል ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ።
ዐቃቤ ህግ ባቀረበው አቤቱታ፣ በተጠርጣሪው ላይ የሚፈለገው የገንዘብ መጠን 3,110,249.74 (ሶስት ሚሊዮን አንድ መቶ አስር ሺህ ሁለት መቶ አርባ ዘጠኝ ከሰባ አራት ሳንቲም) መሆኑን ጠቅሶ፣ ይህ ገንዘብ መያዙ ከተረጋገጠ በሌሎች ባንኮች ላይ ያለው እግድ እንዲነሳ ጠይቋል።
ፍርድ ቤቱ ባደረገው ማጣራት፣ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን በግሎባል ባንክ ስቴድየም ቅርንጫፍ በሚገኘው የሒሳብ ቁጥር 1092116957672 ስር ተይዞ እንዲቆይ ባዘዘው መሰረት ባንኩ ማገዱን አረጋግጧል።
በዚህም መሰረት በግሎባል ባንክ የታገደው የተወሰነ የገንዘብ መጠን ጸንቶ እንዲቆይ እና ከዚህ ውጭ በሌሎች ባንኮች እና በተጠቀሰው የሂሳብ ቁጥር ላይ የሚገኝ ትርፍ ገንዘብ ግን እግዱ እንዲነሳ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

3 months ago