Logo
FastMereja
ኦሮሚያ ባንክ ለስድስት ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ አደረገ!
#fastmereja I በሀገራችን የሚንቀሳቀሱ የግል ባንኮች ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት ረገድ የሚጠበቅባቸውን ሚና እየተጫወቱ የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ቀዳሚ የሆነው ኦሮሚያ ባንክ፣ 1447ኛውን የታላቁን የረመዳን ወር ምክንያት በማድረግ ለተለያዩ ሀገር በቀል ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች የገንዘብና ድጋፍ አድርጓል።

ባንኩ በዛሬዉ እለት ማክሰኞ መጋቢት 08 ቀን 2018 ዓ.ም በዋና መስሪያ ቤቱ ባከናወነው የድጋፍ መርሃ-ግብር፣ በተለይ አቅመ ደካሞችን፣ ወላጅ አልባ ህጻናትን እና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ችግር ላይ የወደቁ ወገኖችን ለሚረዱ ስድስት ድርጅቶች እውቅናና ድጋፍ ሰጥቷል።

በዕለቱ በተካሄደው መርሀ-ግብር ላይ ድጋፍ የተደረገላቸው ድርጅቶች ሰፊ ማህበራዊ ስራዎችን የሚሰሩ እንደሆነም ተገልጿል።
በዛሬዉ እለት ድጋፍ የተደረገላቸዉ ድርጅቶች:-

1. አወሊያ የእርዳታና ልማት ድርጅት (Awolia Relief and Development Organization): የ1,000,000ብር ድጋፍ ተደርጓል።

2.አል-አማና ሁቡል አይታም ወልመሳኪን አብዱልፈታህ ፋውንዴሽን፦የ750,000ብር ድጋፍ ተደርጓል።

3. እገረፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት (Egeref Charitable Organization):-የ500,000ብር ድጋፍ ተደርጓል።

4. ኡሙት የእስልምና በጎ አድራጎት ድርጅት (Umut Islamic Charity Organization):- የ500,000ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡

5. ኢህሳን ፋውንዴሽን (Ihsan Foundation)፦ የ500,000ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡

6. መርሀባ ኸዳም ኢስላሚክ አሶሲዬሸን (Merhaba Khadam Islamic Association):-የ500,000ብር ድጋፍ ተደርጓል።

የኦሮሚያ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተፈሪ መኮንን እንደገለጹት፣ ባንኩ ትርፋማነትን ብቻ ሳይሆን የማህበረሰቡን ችግር መጋራትን እንደ ዋነኛ እሴቱ የሚቆጥር ሲሆን "ይህ የረመዳን የሰደቃ መርሃ-ግብር ባንኩ ለወገኖቹ ካለው አጋርነት ውስጥ አንዱ ማሳያ ነው'' ሲሉ ገልጸዋል።

ኦሮሚያ ባንክ ከዚህ ቀደም ለጤና ተቋማትና ለትምህርት ጥራት የሚውሉ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን፣ አሁንም ይሄው ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመልክቷል።
#ማህበራዊ

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.