ኢራን ሁለት የህንድ የጋዝ ጫኝ መርከቦች በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ እንዲያልፉ ፈቀደች
ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ የዓለም የኃይል አቅርቦት ተቋርጦ በቆየበት በዚህ ወቅት፣ ሁለት የህንድ የፈሳሽ ጋዝ (LPG) ጫኝ መርከቦች በወሽመጡ እንዲያልፉ ልዩ ፈቃድ መስጠቷ ተሰማ።
ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ አራት ምንጮችን ጠቅሶ የዜና ወኪሎች እንደዘገቡት፣ "ሺቫሊክ" (Shivalik) የተሰኘችው የመጀመሪያዋ የህንድ መርከብ በህንድ ባህር ኃይል ታጅባ ወሽመጡን መሻገር ችላለች።
"ናንዳ ዴቪ" (Nanda Devi) የተሰኘችው ሁለተኛዋ መርከብ ደግሞ በሚቀጥሉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ ወሽመጡን እንደምትሻገር ይጠበቃል።
ኢራን በስትራቴጂካዊው የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በጣለችው እገዳ የዓለም የነዳጅ እና የጋዝ ዝውውር ላይ ከፍተኛ መስተጓጎል መፈጠሩ ይታወሳል።
አሁን ለህንድ መርከቦች የተሰጠው ይህ የመለፍያ ፈቃድ፣ ኢራን ካለችበት ጥብቅ አቋም አንጻር እንደ ብርቅዬ አጋጣሚ ተወስዷል።
የህንድ ባህር ኃይል መርከቦቹን እያጀበ መሆኑም የሁለቱን አገራት ግንኙነት እና የባህር ላይ ደህንነትን ለማረጋገጥ የተደረገ ጥረት ተደርጎ ተቆጥሯል።
seledadotio

3 months ago