ሰሜን ኮሪያ 10 የሚጠጉ የባሊስቲክ ሚሳይሎችን መተኮሷ ተነገረ
የደቡብ ኮሪያ ጦር ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ ሰሜን ኮሪያ 10 የሚጠጉ አጫጭር ርቀት ተኳሽ የባሊስቲክ ሚሳይሎችን ወደ ምስራቃዊ የባሕር ጠረፏ መተኮሷን አስታውቋል።
አል አረቢያ የደቡብ ኮሪያን የጦር ኃይሎች ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ሚሳይሎቹ የተተኮሱት ከሰሜን ኮሪያ ዋና ከተማ ፒዮንግያንግ አቅራቢያ ካለው የሱናን አካባቢ ነው።
እነዚህ ሚሳይሎች ወደ 350 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ ርቀት ከተጓዙ በኋላ በምስራቃዊው የባሕር ክፍል (የጃፓን ባሕር) ላይ ማረፋቸውን የደቡብ ኮሪያ የጋራ ኤታማዦር ሹም ገልጸዋል።
የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ባለሥልጣናት ድርጊቱን "ግልጽ ትንኮሳ" ሲሉ የጠሩት ሲሆን፤ ጥቃቱን ተከትሎ ከጃፓን እና ከአሜሪካ ጋር በመተባበር ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተሉ መሆኑን አስታውቀዋል።
ይህ መጠነ ሰፊ የሚሳይል ሙከራ የተደረገው፤ ሰሜን ኮሪያ ከጥቂት ቀናት በፊት ወታደራዊ የሰላዮች ሳተላይት ወደ ህዋ ለማምጠቅ ያደረገችው ሙከራ መክሸፉን ተከትሎ መሆኑ ትኩረት ስቧል።
ፒዮንግያንግ በቅርቡ በቆሻሻ የተሞሉ ፊኛዎችን ወደ ደቡብ ኮሪያ ድንበር በመላክ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ውጥረት ይበልጥ አባብሳው እንደነበር ይታወሳል።
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ በበኩላቸው፤ ሰሜን ኮሪያ የባሊስቲክ ሚሳይል በመተኮስ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎችን ጥሳለች ሲሉ ድርጊቱን አውግዘዋል።
ልዑል ወልዴ

5 months ago