የኢትዮጵያ ስፔሻል ኦሎምፒክ ሀገር አቀፍ ወድድር በድምቀት ስፖርታዊ ውድድር በድምቀት ተከፈተ
#ethiopia | 11ኛው የዓለም የዳውን ሲንድሮም ቀን በኢትዮጵያ “Let me win, but if I cannot win, let me be brave in the attempt" ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀዉ ስፖርታዊ ዉድድር በዛሬዉ እለት በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በይፋ ተከፍቷል።
በዛሬዉ የመክፈቻ ስነ-ስርአት ላይ በባህልና ስፖርት ሚንስትር የስፖርትና ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ ክቡር መኪዩ መሀመድ :
በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በስፖርት ማህበራት ምዝገባ ፣ ድጋፍ እና ቁጥጥር መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳንኤል ዳኜ : የኢትዮጵያ ስፔሻል ኦሎምፒክ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ግርማ ዘውድ: የኢትዮጵያ ስፔሻል ኦሎምፒክ ብሄራዊ ፅህፈት ቤት ሃለፊ የሆኑት ወ/ሮ ትርስተወልድ አበባ አየሁን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች እና ከተለያዩ ክልሎች ተሳታፊ ስፖርተኞችና አመራሮች በተገኙበት ወድድሩ በድምቀት ተከፍቷል።
ስፔሻል ኦሊምፒክስ ኢትዮጵያ ከ“ፍቅር የኢትዮጵያ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ብሔራዊ ማኅበር” ጋር በመተባበር የተዘጋጀዉ ይህ ሀገር አቀፍ ጨዋታ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።
ዉድድሩ ሁሉንም የኦሎምፒክ ስፖርት ዓይነቶች ያካተተ ሲሆን፣ ውድድሩም የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸውን ተወዳዳሪዎች ባማከለ ልዩ የስፖርት ሕግ መሠረት እየተከናወነ ይገኛል።
የፍቅር ኢትዮጵያ ማህበር የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸውን ልጆች አስተምሮና አሰልጥኖ በማኅበሩ ውስጥ የሥራ ቅጥር እንዲያገኙ በማድረግ ጭምር አርአያነት ያለው ሥራ እያከናወነ ይገኛል።
በአሁኑ ወቅት በአፍሪካና በኢትዮጵያ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው ወገኖች ላይ የሚደርሰው መገለልና መድልዎ ከፍተኛ በመሆኑ፣ እንዲህ ያሉ ስፖርታዊ መድረኮች ግንዛቤን ለመፍጠርና ብቸኝነትን ለመቀነስ ትልቅ ፋይዳ አላቸው።
በዛሬዉ የመክፈቻ መርሀ-ግብር ላይ ፊልም ደራሲ፣ዳይሬክተር እንዲሁም ፕሮዲዉሰር የሆነችዉን የራስወርቅ ግርማ የስፔሻል ኦሎምፒክ በጎ ፍቃድ አምባሳደር በመሆን ተሹማለች ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

5 months ago