Logo
YenetaTube
የእውቀት ማህደር ውስጣቸው ተቀብሯልና ልጆቻችን ትምህርት ቤት ያግኙ!
ይህ የሆፕ ኤስቢኤች ጥሪ ነው።

ይህን ያለው ደግሞ በ2026 ብሔራዊ የአፈጣጠር ችግር ዘመቻ ከጤና ጥበቃ ጋር ያደረገውን ንቅናቄ ማጠናቀቁን ተከትሎ ነው።

በተለይ በህብለሰረሰር ዘንግ ክፍተት የአፈጣጠር ችግር( Spina Bifida and Hydrocephalus) ያለባቸውን ከ6000 በላይ ህፃናት ድጋፍ እያደረገ ያለው HOPE-SBH ልጆቼ መ ማር እየቻሉ እድሉን አለማግኘታቸው እንደአገር ሊታሰብበት ይገባል ብሏል።

HOPE-SBH (ሆፕ ኤስ.ቢ.ኤች) ባለፉት ሳምንታት ብቻ

በብሔራዊ ደረጃ
-የአፈጣጠር ችግሮች ዘመቻ ሀገር አቀፍ ዝግጅቶችን ለማድረግ ከኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር

በአዲስ አበባ
- ከሶስት ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ከ200 የሚበልጡ ተማሪዎችን ከመገናኛ ብዙሃን፣ ከፓርላማ አባላት፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከአርቲስቶች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን ያሳተፈ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅት አዘጋጅቷል።

- በስፒና ቢፊዳ እና ሀይድሮሴፋለስ የተጎዱ ቤተሰቦች ከፊዚዮቴራፒ፣ ከአእምሮ ጤና እና የንግግር ህክምና የባለሙያዎች አገልግሎት ሆፕ ኤስ.ቢ.ኤች ውስጥ ሁለገብ እንክብካቤ ድጋፍ ጊዜ አካሂዷል።

- በአዲስ አበባ ከጤና ሚኒስቴር እና ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር የአዲስ አበባን የአፈጣጠር ችግር ዘመቻ መክፈቻ እና ግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅት አድርጓል።

በአፋር ክልል
- በክልሉ ስላሉት ስፒና ቢፊዳ እና ሀይድሮሴፋለስ ችግር እና ሊወሰዱ የሚገቡ ዘርፈ ብዙ እርምጃዎች ላይ ለመወያየት ከዋና ዋና ባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል።

- በዱብቲ 1500 የትምህርት ሰጪ ቁሳቁሶችን በማሰራጨት ህብረተሰቡን ያሳተፈ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ አካሂዷል።

የኦሮሚያ ክልል
- ከኦሮሚያ ከጤና ሚኒስቴር እና ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር በክልል ደተጃ የአፈጣጠር ችግሮች ዘመቻ አካሂዷል።

-በጅማ ከተማ ለሁለት ቀናት የቆየ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እንዲሁም 1,500 የትምህርት ቁሳቁሶችን በማሰራጨት ህብረተሰቡ በንቃት እንዲሳተፉ አስችሏል።

- የነርቭ ዘንግ ክፍተቶችን የመከላከል እና የመንከባከብ ስራን በማጠናከር ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት በጅማ ከተማ አዘጋጅቷል።

በሲዳማ ክልል
- ከሲዳማ ጤና ጥበቃ ቢሮ ጋር በመተባበር የወሊድ መጓደል/የአፈጣጠር ችግ ዘመቻ ክልላዊ የመክፈቻና መዝጊያ ዝግጅቶችን አድርጓል።

የአማራ ክልል
-የአፈጣጠር ችግሮች ዘመቻ ክልላዊ የመዝጊያ ዝግጅቶችን ለማድረግ ከአማራ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር
- በዘመቻው ወቅት ለተደረጉ ቀዶ ጥገናዎች በአይነት ድጋፍ ተደረገ።

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር

- በዘመቻው ወቅት የአከርካሪ አጥንት እና የሃይድሮሴፋለስ ጉዳቶችን እና አራት የነርቭ ቀዶ ጥገና ዎች እንዲካሄዱ አመቻችቷል።

- ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተውጣጡ በርካታ ተሳታፊዎችን ያሳተፈ በSpina Bifida እና Hydrocephalus ዙሪያ አውደ ጥናት አካሂዷል።

-በከተማው በሚገኙ ሁለት አካባቢዎች ለሶስት ቀናት የሚቆይ የህዝብ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ሰርቷል። 2,000 የትምህርት መስጫ ቁሳቁሶችን በሶስት የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች አከፋፍሏል።

በዝግጅቱ ማጠቃለያ ላይ የሆፕ ኤስ.ቢ.ኤች መስራችና ባለራእይ ወ/ሮ ቤዛ በሻህ የእውቀት ማህደር ውስጣቸው ተቀብሯልና ልጆቻችን ትምህርት ቤት ያግኙ! የሚል መፈክር አሰምተዋል።

ሆፕ ኤስ.ቢ.ኤች አሁንም በጉዳዩ ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ የጠቆመ ሲሆን ለዚሁና መሰል ድጋፎች ላደረገው አስተዋፅኦ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የእውቅና ሽልማት ተርክቶለታል።

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.