Logo
Getu Temesgen
OBN ለኢትዮጲያ ፕሪሚርሊግ 200 ሚሊዮን ብር ይከፍላል:

ክለቦች ስንት ያገኛሉ?
#ethiopia | ከአምስት አመታት ቆይታ በኋላ ከዲኤስቲቪ ሱፐር ስፖርት ጋር የተለያየዉ የኢትዮጲያ ፕሪሚርሊግ አክሲዮን ማህበር ዘንድሮ ፊቱን ወደ ሀገር ዉስጥ የቴሌቪዥን ጣቢያ በማዞር የሊጉን የምስል መብት ለOBN ለሁለት አመት ሸጧል።

OBNየሊጉን የምስል መብት ለሁለት አመት በሁለት መቶ ሚሊዮን ብር እንደገዛዉ ብስራት ራዲዮ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸዉ ሰዎች ሰምቷል።

ይህንንም ተከትሎ ዘንድሮ OBN 100 ሚሊዮን ብር የሚከፍል ሲሆን ክለቦች ከምስል ሽያጩ የሚያገኙት ገንዘብ ከዚህ ቀደም ከነበረዉ በእጂጉ ያነሰ እንደሚሆን ተገምቷል።

ከ100 ሚሊየኑ ዉስጥ ክለቦች ሊያገኙት የሚችሉት ገንዘብ ከግማሽ በታች ሊሆን እንደሚችል ሲተነበይ ምክንያቱ ደግሞ ከሚገኘዉ ገንዘብ ላይ የሊጉ አክሲዮን ማህበር ለዳኞች እና ለልዩ ልዩ ወጪዎች ቀንሶ ተራፊዉን ስለሚያከፋፍል እንደሆነ ታዉቋል።

በአምናዉ የዉድድር ዘመን በሀገሪቱ ከታየዉ ዶላር ጭማሪ ጋር ተያይዞ አክሲዮን ማህበሩ በሊጉ ታሪክ ከፍተኛ የተባለዉን ገንዘብ ለክለቦች ሲያከፋፍል የአምናዉ ሻምፒዮን ኢትዮጲያ መድን 40 ሚሊዮን ብር እንዳገኘ የሚዘነጋ አይደለም።

ዘንድሮ ግን ሻምፒዮን የሚሆነዉ ክለብ ምን አልባትም ከአምስት ሚሊዮን ብር በታች ሊያገኝ እንደሚችል ይገመታል ።

የኢትዮጲያ ፕሪሚርሊግ አክሲዮን ማህበር አምና ከ409 ሚሊዮን ብር በላይ ለ15 ክለቦች ሲያከፋፍል ዘንድሮ ግን ምን አልባትም ለ20 ክለቦች ከ50ሚሊዮን ብር ያነሰ ገንዘብ ያከፋፍላል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ብስራት ሬዲዮ ዘግቧል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.