Logo
Getu Temesgen
በ4.3 ቢሊዮን ብር እየተገነባ የሚገኘው 4ኛው ምዕራፍ የመልሶ ግንባታና ዓቅም ማሳደግ ፕሮጀክት
#ethiopia | በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተሞች ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አስተማማኝ ለማድረግ በ4.3 ቢሊዮን ብር 4ኛው ምዕራፍ የዲስትሪቡዩሽን መስመር መልሶ ግንባታና ዓቅም ማሳደግ ፕሮጀክት እየተከናወነ ይገኛል፡፡

703 ኪ.ሜ የዲስትሪቡሽን ኔትዎርክ መልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግን ያካተተው ይህ 4ኛው ምዕራፍ ፕሮጀክት፤ 2 ሺህ አዲስ የተለያየ አቅም ያላቸውን ትራንስፎርመሮች ተከላና 2 ሺህ ነባር ትራንስፎርመሮችን አቅም የማሳደግ ሥራ የሚከናወንበት ይሆናል፡፡

በፕሮጀክቱ ከኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ወጪ የሚሆኑ 56 ማሰራጫ መስመሮችን መልሶ የመገንባትና የማሻሻል እንዲሁም ከተፈቀደው የኃይል አጠቃቀም በላይ ሲሆን መቆጣጠር የሚያስችሉ 62 የሎድ ብሬክ ስዊች ገጠማ ይከናወናል፡፡

በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ አጠቃላይ የፊዚካል ሥራው አፈፃፀም 36 ነጥብ 74 በመቶ የደረሰ ሲሆን፤ 2 ሺህ 857 የኮንክሪት ምሰሶዎች ተከላ ስራም ተከናውኗል፡፡

ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በአዲስ አበባና በሸገር ከተሞች በዓመት በ100 ኪ.ሜ የመካከለኛ የኃይል ማሰራጫ መስመር ላይ የሚከሰተውን የኃይል መቆራረጥ ድግግሞሽን በ27 በመቶ ለመቀነስ ያስችላል፡፡ እንዲሁም የትራንስፎርመር መቃጠልን ከ3 ወደ 2 በመቶ ለመቀነስ ያስችላል ተብሎ ይጠብቃል።

የሚገነቡት የዲስትሪቡዩሽን መስመሮች በኮንክሪት ምሰሶና በሽፍን ኬብል በመሆኑ አደጋን ለመከላከልና ረጅም ዓመት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ናቸው፡፡

ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ አጠቃላይ ወጪ 4.3 ቢሊዮን ብር ሲሆን፤ ጠቅላላ ወጪው የሚሸፈነው ከአለም ባንክ በተገኘ ብድር ነው፡፡

ይህ ፕሮጀክት በአዴሌ (ADELE Project) ከሚሰሩ የመልሶ ግንባታና ማሻሻያ ስራዎች አንዱ ነው፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.