ኢራን ጠቅላይ መሪዋን ልትሰይም ነው፤ እስራኤል መራጮቹን እና ተመራጩን እያደነች መሆኗን ገለጸች
ቀጣዩን የኢራን ጠቅላይ መሪ ለመሰየም እየመከረ ያለው የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ከፍተኛ የሊቃውንት ጉባዔ ከስምምነት ላይ መድረሱ ተነገረ።
ጉባዔው የመጨረሻውን ውሳኔ ለማሳለፍ የጋራ አቋም ላይ መድረሱ አንድ አባሉ ሲናገሩ፣ እስራኤል ደግሞ መራጮችን እና ተመራጩን ዒላማ ማድረጓን እንደምትቀጥል አስታወቀች።
ሞሐመድ መህዲ ሚርባጌሪ ለኢራን ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት “ጽኑ እና የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል” በማለት አንዳንድ መቋጫ የሚሹ ነገሮች ብቻ መቅረታቸውን አመልክተዋል።
የሊቃውንቱ ጉባዔ ትኩረት ሰጥቶ ያለማቋረጥ የሚጠበቅበትን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ ነገር ግን "በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንቅፋቶች አሉ። ለዚህም ሥራዎች በጥንቃቄ ተሠርተው በመግባባት ለታሪክ እንዲቀመጡ ይደረጋል” ብለዋል።
አስካሁን ባለው ሂደት "ግልጽ እና አስተማማኝ የጋራ የሃሳብ አንድነት ላይ ተደርሷል” ያሉት የጉባዔው አባል “እንቅፋቶች” ያሏቸው ጉዳዮችም በፍጥነት እንደሚወገዱ ተስፋቸውን ገልጸዋል።
የኢራን ከፍተኛ ሊቃውንት ቀጣዩን መሪ ለመምረጥ የሚያከናወኑትን ተግባር በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን የገለጸችው እስራኤል ደግሞ የአያቶላህ አሊ ኻሜኒን የሚተካውን መሪ ማደኗን እንደምትቀጥል አስጠንቅቃለች።
የእስራኤል ጦር በፋርስ ቋንቋ [የኢራን ብሔራዊ ቋንቋ] በኤክስ ላይ ባሰፈረው ጽሑፍ “ለአስርታት ተሰብስቦ የማያውቀው የኢራን የሊቃውንት ጉባዔ፣ በቆም ከተማ ውስጥ በቅርቡ ስብሰባውን ያደርጋል።
"ልንነግራችሁ የምንፈልገው ጠቅላይ መሪውን ለመተካት የሚፈልገውን እና ተተኪውን ለመሰየም የሚጥሩትን ሰዎች በሙሉ እስራኤል ማደኗን ትቀጥላላች።
"ተተኪውን መሪ ለመምረጥ በሚደረገው ስብሰባ የሚሳተፉትን በሙሉ ዒላማ ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማንል ልናስጠነቅቃችሁ እንፈልጋለን። ይህ ማስጠንቀቂያ ነው!” በማለት የሚመረጠውን መሪ ብቻ ሳይሆን በምርጫው የሚሳተፉትን ከማጥቃት ወደኋላ እንደማትል እስራኤል አስታውቃለች።
ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃት በጀመሩ በመጀመሪያው ሰዓት ላይ ነበር የአገሪቱ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ኻሜኒ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት የተገደሉት።
BBC

3 months ago