የዳውን ሲንድሮም ቀን በሀገር አቀፍ የስፖርት ውድድር ይከበራል
#ethiopia | ስፔሻል ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ ከፍቅር የኢትዮጵያ የአእምሮ እድገት ውስንነት ካላቸው ዜጎች ወላጆች ብሔራዊ ማህበር ጋር በመተባበር፣ የዓለም የዳውን ሲንድሮም ቀንን ምክንያት በማድረግ ሀገር አቀፍ የስፖርት ውድድር ሊያካሂድ ነው።
"በብቸኝነት ላይ በጋራ እንመክት" በሚል ዓለም አቀፍ መሪ ቃል የሚካሄደው ዝግጅት፣ ከፊታችን መጋቢት 4 እስከ 6 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በድምቀት እንደሚከናወን ተገልጿል።
እንደ ማህበሩ መረጃ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ መጋቢት 12 የሚከበረው የዳውን ሲንድሮም ቀን፣ በኢትዮጵያ ለ11ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን፤ ዋና ዓላማውም
የአእምሮ እድገት ውስንነትና ዳውን ሲንድሮም ያለባቸው ዜጎች ያላቸውን የተፈጥሮ ብቃትና ክህሎት ለህዝብ ማሳየት፣በማህበረሰቡ ዘንድ ያለውን የተሳሳተ ግንዛቤና መገለልን ማስወገድ፣ልጆቹ ከቤት ወጥተው ከሌሎች እኩዮቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉና ሁለንተናዊ ሰብአዊ መብቶቻቸው እንዲከበሩ ግንዛቤ መፍጠር ነው።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከ5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች የአእምሮ እድገት ውስንነት እንደሚኖርባቸው የሚገመት ሲሆን፣ ማህበሩ እነዚህ ዜጎች በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና በባህላዊ መብቶች እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከሚመለከታቸው የመንግስትና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።
በኢትዮጵያ አካዳሚው በሚካሄደው በዚህ ሀገር አቀፍ ውድድር ላይ ከተለያዩ ክልሎች የተወጣጡ ስፖርተኞች፣ ወላጆችና የዘርፉ ባለሙያዎች የሚታደሙ ሲሆን፤ ዝግጅቱ የአካል ጉዳተኝነትን አስመልክቶ በዓለም አቀፍ ደረጃ የፀደቁ (UNCRPD) ስምምነቶችን በተግባር ለመተርጎም ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ታምኖበታል።
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን
#downsyndromedayethiopia #specialolympicsethiopia #inclusionmatters #togetheragainstloneliness #intellectualdisabilityawareness

5 months ago