በኢራን 165 ተማሪዎች የተገደሉበትን ጥቃት ተከትሎ በኢሚሬትስ የሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር በሚሳይል ተመታ
የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በደቡባዊ ኢራን በሚገኝ የሴቶች ትምህርት ቤት ላይ ለደረሰው አውዳሚ ጥቃት ምላሽ ለመስጠት፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚገኘውን "አል ዳፍራ" የተሰኘ የአሜሪካ የጦር ሰፈር መምታቱን አስታወቀ።
እንደ ፋርስ የዜና ወኪል ዘገባ፣ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በኢራን በሚገኘው "ሻጃሬ ታጄቫ" የሴቶች ትምህርት ቤት ላይ በደረሰው ጥቃት 165 ተማሪዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 171 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።
የአብዮታዊ ዘብ ባወጣው መግለጫ፣ ይህን "አሸባሪ" የተባለውን ጥቃት የፈጸሙት የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች የተነሱት ከአል ዳፍራ የጦር ሰፈር መሆኑን ገልጿል።

5 months ago